የካፈቾ ብሔር የዘመን መለወጫ (የቤኔ ሻዴዬ ባሮ) በቦንጌ ሻንበቶ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።
የካፈቾ ብሔር የጥንት ታሪክና የዳበረ ባህል ባለቤት ነው። ከዘመን ዘመን ተሻግሮ ለዚህ ትውልድ የደረሱ የተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች አሏቸው። ከነዚህም አንዱ ዛሬ በደማቅ ሁኔታ በቦንጌ ሻንበቶ እየተከበረ ያለው የአዲስ ዓመት የዘመን መለወጫ “የቤኔ ሻዴዬ ባሮ”በዓል ነው። የቤኔ ሻዴዬ ባሮ በካፈቾዎች ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው የብሔሩ ታላቅ ዕሴትና የማይዳሰስ ቅርስ ነው። የካፋ ህዝብ ዘመን አቆጣጠር የአዝመራ ወቅትን…
