የፌደራል ሱፐርቪዥን ቡድን በክልሉ በቤንች ሸኮ ዞን በደቡብ ቤንች ወረዳ እየተሰሩ ያሉትን የልማት ስራዎችን ጎበኘ ።

በፕላንና በልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር በዶ/ር ፍጹም አሰፋ የተመራ የፌደራል ሱፐርቪዥን ቡድን በቤንች ሸኮ ዞን በደቡብ ቤንች ወረዳ ግብርና ልማት ስራ ጃንቹ የመዝ ክላስተር እርሸ፣ በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አቢይ አህመድ መሠረተ ድንጋይ ተቀምጦ ወደስራ የተገበውን የደንቢ ገበታ ለትውልድ የፕሮጀክት አፈፃፀም ያለበት ደረጃ እና በሌማት ትሩፋት ውጤቶችአንዱ አካል የሆነው የማር ምርት ተመልክቷል። በደቡብ ቤንች በ200 አርሶአደሮች…

Read More

የመደመር ትውልድ መጽሐፍ በትረካ ለአድማጭና ተመልካች ሊቀርብ ነው

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው የመደመር ትውልድ መጽሕፍ በትረካ፣ በዘጋቢ ፊልምና በሌሎች አማራጮች ለአድማጭና ተመልካቾች ሊቀርብ ነው። አዲስ ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ትረካና ሌሎች ፓኬጆች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡ በመርሐ ግብሩ የቱሪዝም ሚኒስትር ደኤታ ሌንሳ መኮንን፣ የውጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃፋር በድሩ፣ የአዲስ ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ መሃመድ…

Read More

የክልሉ ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የጤና ተቋማት አገልግሎት ብቃት ማሳደግ ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የክልሉ መንግስት ረዳት ተጠሪ አሳሰቡ።

በክልሉ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም አተገባበርን ለማሻሻል የሚመክር መድረክ በታርጫ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል ። በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ መንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ በላይ ተሰማ አምራች እና ጤናማ ማህበረሰብ የመገንባት ሂደት ስኬታማ ሊሆን የሚችለው የጤና ተቋማት አገልግሎት እና አደረጃጀት ሲገነባ ነው። ስለሆነም በክልሉ በየደረጃ የሚገኙ የመንግስት መዋቅሮችና አደረጃጀቶች እንዲሁም የህብረተሰብ ክፍሎች የዘርፉን ሥራ ውጤታማ ለማድረግ ርብርብ…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ከኦሮሚያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር የትብብር ስነድ ተፈራረመ

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልል መንግሥት፤ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል የጋራ ውይይት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾና የክልሉ የካቢኔ አባላት በተገኙበት አድርገዋል። በሁለቱ አጎራባች ክልሎች ለዘመናት የዘለቀው ጠንካራ ማህበራዊ መስተጋብር እንዲሁም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዳለ ያወሱት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ይህን መልካም ግኑኝነት ወደ ልማት…

Read More

ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ከኢቢሲ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ዋና ስራ-አስፈፃሚና ከሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ በክልሉና በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን መካከል ያለውን ግንኝነት ማጠናከር ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ። ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት ኢቢሲ ህዝብና መንግሥትን በማቀራረብ እንዲሁም ከህዝብ የሚነሱ ጥያቄዎችን ሚዛናዊ…

Read More

“ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና!”

“ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ አባላት ኮንፈረንስ ከመሠረታዊ ድርጅት እስከ ክልል ከመጋቢት 8-14 /2016 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል። በክልል በሁሉም ዞን ፣ወረዳ ፣ከተማ እና ቀበሌ /መሠረታዊ ድርጅት እንዲሁም በክልል ማዕከል የማጠቃለያ ፣ የተሳካ፣ ደማቅ እና በዓይነቱ ልዩ የሆነ የአባላት ኮንፈረንስ ለማድረግ የቅድመ-ዝግጅት ስራ የተሰራ ይገኛል። ፓርቲያችን በስድስተኛው…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለአምስት ተቋማት ‘የኢትዮጵያ ተቋማት ስኬት ሽልማትን’ አበረከቱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ በአድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደ ደማቅ ስነ-ስርዓት ለአምስት ተቋማት ‘የኢትዮጵያ ተቋማት ስኬት ሽልማትን’ አበርክተዋል። በሽልማቱ የከበሩት ተቋማት የግብርና ሚኒስቴር/በስንዴ ልማት ፕሮግራም/፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መሆናቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ተቋማቱ የኢትዮጵያ የእድገት እና የፈጠራ ልክ ማሳያ…

Read More

የክልሉ የስፖርት ፌዴሬሽኖች የሚያደርገው የጋራ ውይይት መድረክ በታርጫ ከተማ ተካሄደ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ከክልሉ የስፖርት ፌዴሬሽኖች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አመራሮች፣ የክልሉ ስፖርት ፌዴሬሽኖች ፕረዚዳንቶችና ምክትል ፕረዚዳንቶች፣ የባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሃላፊዎች፣ የዞን ፋሲሊቲና አደረጃጀት ሥራ ሂደት ቡድን መሪዎች፣ የቢሮ የስፖርት ዘርፍ ዳይሬክተሮች፣ ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። የምክክር መድረኩ…

Read More

በክልሉ በመደማመጥ፣ በመከባበርና በመመካከር የተረጋጋ የፖለቲካ ስነ- ምህደር መፍጠር መቻሉን ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለጹ

የፌዴራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከወከላቸው ህዝብ ጋር ያደረጉት የውይይት ግብረ-መልስ ለክልሉ ካቢኔ አካላት በቦንጋ ከተማ አቅርበዋል። በመድረኩ በክልሉ የተጀመሩ የሠላምና ፀጥታ ንቅናቄ መድረኮች ውጤታማ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተመልክቷል ፡፡ በክልሉ የጤናና የውሃ ፕሮጀክቶችን ለማንቀሳቀስ እና በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ለመጨረስ የሚደረገው ጥረት እጅግ አበረታች መሆኑ ተገልጿል፡፡ የተጀመሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም…

Read More

ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካን እየጎበኙ ነው

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ የሚገኘውን የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካን እየጎበኙ ነው፡፡ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የማዕድን ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) እና ሌሎች የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በጉብኝቱ እየተሳተፉ ነው ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

Read More