Trendings

በእገታ፣ በዘረፋ እና በተለያዩ ወንጀሎች ተሳትፈዋል የተባሉ 12 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ::

በእገታ፣ በዘረፋ እና በተለያዩ የማጭበረበር ወንጀሎች የተሳተፉና የተለያዩ 16 የወንጀል ዓይነቶችን የፈፀሙ በአንድ ቡድን የተደራጁ 12 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ የፌደራል ፖሊስ ገለጸ፡፡ በፌደራል ፖሊስ የሚመራው የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ውጤት እያስመዘገበ ተጠናክሮ መቀጠሉን ፖሊስ ገልጿል። ፖሊስ በመግለጫው ፥ በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከጥር 29 እስከ አሁን በቀጠለው ኦፕሬሽን በቁጥጥር ሥር…

Read More

ከሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ኢንቨስትመንት ላስመዘገቡ አራት ኩባንያዎች የማዕድን ማምረት ፈቃድ ተሰጠ

የፍቃድ ስምምነቱን የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ እና የኩባንያዎቹ ስራ አስፈጻሚዎች ተፈራርመዋል፡፡ ፈቃድ የተሰጣቸው ኩባንያዎች የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 27ኛ መደበኛ ስብሰባ የብሮሚን፣ የግራናይት፣ የድንጋይ ከሰል እና የደለል ወርቅ ማዕድናትን ለማልማት በተወሰነው ስምምነት መሰረት ነው፡፡ ለኩባንያዎቹ ፈቃድ የተሰጠው የማዕድን ምርመራ ፈቃድ ወስደው የምርመራ ስራ በመስራት እና ከእዚህ በፊት የተሰሩ ጥናቶችን መረጃ በመጠቀም ወደ ምርት መግባት…

Read More

በሞስኮ ከደረሰው የሽብር ጥቃት በኋላ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሰብአዊነት እና የምህረት ጥሪ አቅርበዋል::

በክሮከስ የከተማ አዳራሽ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ባደረጉት ንግግር የሰብዓዊነት እና የምህረት አስተሳሰቦች ልዩ ጠቀሜታ አላቸው ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት በሞስኮ የህግ አውጭዎች በአሸባሪዎቹ ላይ የሞት ቅጣት ለመወሰን ህጉን ወደነበረበት ለመመለስ ክርክር መግጠማቸውን ተከትሎ ነው። በክሬምሊን ለወጣት አርቲስቶች እና አስተማሪዎች ክብር ለመስጠት በተዘጋጀ ስነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ፑቲን፤ ባለፈው አርብ በሞስኮ የሙዚቃ ድግስ…

Read More

በሚዛን አማን ከተማ በአራት ቀበሌዎች 1 ሺህ 148 ይዞታዎች ወደ ህጋዊ ትግበራ መግባታቸው ተገለጸ ።

በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የሴፍትኔት ፕሮግራሞች እና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ዙሪያ ምልከታ ተደርጓል ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር የማታለም ቸኮል በከተማ አስተዳደር ተገኝተው ምልከታ አድርገዋል። በምልከታው ወቅት የከተማው ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ቤሪ እንደገለጹት በክልሉ ደንብና መመሪያ ወጥቶ በስራ ላይ የሚገኘው ሳይፈቀዱ የተያዙ…

Read More

300 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል ያለው የቻይና ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ::

300 ሚሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት ካፒታል ያለው ዌንዡ ኒክሲን ትሬዲንግ ኩባንያ፤ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ወረቀት የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የኩባንያውን አመራሮች በፅሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። የኩባንያው አመራሮች ስለ ኢንቨስትመንት ዕቅዳቸው ዝርዝር መረጃዎችን ማቅረባቸው ተጠቅሷል። የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ፤ በኮርፖሬሽኑ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ማዕከሎችን፤ማበረታቻዎችን እንዲሁም የመሰረተ ልማትና የአገልግሎት አሰጣጥን…

Read More

ኢትዮጵያ በ13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች ስፖርተኞች ባስመዘገቡት አኩሪ ውጤት ኮርታባቸዋለች::

በ13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች ስፖርተኞች ፈታኙን ሞቃታማ የአየር ንብረት በመቋቋም ባስመዘገቡት አመርቂ ውጤት ኢትዮጵያ ኮርታባቸዋለች ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ ገለጹ። በጋና በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች ስምንተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል። ልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳን ጨምሮ በሚኒስቴሩ የስፖርት…

Read More

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በቦንጋ ከተማ ስልጠና መስጠት ጀመረ::

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር በልዩ ሁኔታ ለተመረጡ ኢንተርፕራይዞችና ባለሀብቶች ለ 5 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ስልጠና በቦንጋ ከተማ መስጠት ጀምሯል። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አስፋው አበራ በዙም ባስተላለፉት መልዕክት የአሁኑ ስልጠና ከዚህ ቀደም ከነበረው የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና የተለየ መሆኑን ተናግረዋል ። ለዚህ…

Read More

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ያልመለሱ 565 ግለሰቦች የስም ዝርዝር ይፋ አደረገ::

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በባንኩ የሲስተም ማዘመኛ ሥራ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በሂሳብችሁ ከተቀመጠ ገንዘብ ውጭ በሕገወጥ መንገድ ገንዘብ የወሰዳችሁ ግለሰቦች በፈቃደኝነት ሂሳባችሁ በሚገኝበት ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ ወይም ዲጂታል የክፍያ ዘዴን በመጠቀም ገንዘቡን እስከ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ተመላሽ እንዲያደርጉ መጠየቁ ይታወሳል። በዚህ መሰረት 14441 የሚሆኑ ግለሰቦች በተሰጠው ጊዜ…

Read More

ተቋርጦ የነበረውን የቴፒ አይሮፕላን ማረፊያ መልሶ ወደ ስራ ለማስገባት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከማሻ ከተማ ነጋዴዎችና የግል ባለሀብቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ።

የማሻ ወረዳና የከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው ለእቅዱ እውን መሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ዞኑ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት ብቻ ሳይሆን ሰፊ የመልማት እድል ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መሰል የትራንስፖርት አገልግሎት ማስፈለጉን ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ምንም ስልጣኔ ባልተስፋፋበት ወቅት የቴፒ አየር ማረፊያ ከ1950 ዓመተ ምህረት ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ…

Read More

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አለልኝ አዘነ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ::

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። የባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ እንዳስታወቀው፤ አለልኝ በጉዳት ምክንያት ከቡድኑ ተለይቶ በትውልድ ስፍራው አርባ ምንጭ ለእረፍት የሄደ ሲሆን ትናንት ምሽት በድንገት ህይወቱ አልፏል። አለልኝ የእግርኳስ ህይወቱን በአርባምንጭ ከተማ ክለብ የጀመረ ሲሆን በባህርዳር ከተማ ለሁለት ዓመታት ምርጥ ጊዜ…

Read More