በአካል የጠነከረ በአእምሮ የበለፀገ ጤናው የተጠበቀና አምራች ዜጋን መፍጠር ለሀገራችን ሁለተናዊ ብልጽግና ጉልህ ሚና እንዳለው የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ገለፁ
“የጤና ዘርፍ አርበኝነት ለሀገር ዕድገት” በሚል መሪ ቃል በዞኑ ከሚገኙ የጤና ባለሙያዎች፣ ሠራተኞች እና ከባለድርሻ አካላት ጋራ የምክክር መድረክ በዞን ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል። በምክክር መድረክ የተገኙ የዳዉሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ እንደገለጹት የጤናው ዘርፍ ለሀገር ዕድገትና በሁሉም መስክ ሁለተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና አለው ። የጤና ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን በማሻሻል ከማኅበረሰብ የሚነሱ…
