በተቀናጀ 2ኛ ዙር የልጅነት ልምሻ ከ5 መቶ ሺህ 64 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሕጻናት የመከላከያ ክትባት ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
ክልላዊ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በዞኑ ታርጫ ከተማ ተደርጓል። በዚህ ዘመቻ በክልሉ ሁሉም ቀበሌያት የተቀናጀ 2ኛ ዙር የልጅነት ልምሻ በሽታ መከላከያ ክትባት ከግንቦት 22-25/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥም ተገልጿል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራት ቦጋለ እንደገለፁት ይህ የልጅነት ልምሻ በሽታ በብዛት ከሰሃራ በታች ባሉት አገራት የሚታይ በሽታ በመሆኑ በአገር…
