የጤናው ዘርፍ ተግዳሮቶች በመቅረፍ የአገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለጹ።
በዉይይቱ የተሳተፉ የጤና ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት የእነሱን ሚዛናዊ ጥያቄ ለፖለቲካ ዓላማ ለማዋል የሚጠቀሙ አካላት ትክክል እንዳልሆነ ገልጸዉ ከሙያዉ ሥነ ምግባር ባፈነገጠ መልኩ በአንዳንድ ጤና ባለሙያዎች የሚታይ የስራ ማቆም እንቅስቃሴ ትክክል አለመሆኑን ገልጸዋል። ለጤና ባለሙያዎች የተለያዩ የማትጊያ ስልቶችን በማበጀት የጤና ባለሙያዎችን ማበረታታት እንደሚገባ የገለጹት ተሳታፊዎቹ፥ ለጥቅማጥም ጥያቄያቸውም በየደረጃዉ ያለዉ የመንግሥት መዋቅር ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። የጤና…
