በፋይናንስ አሰራር ላይ የሚታዩ ችግሮችን በመፍታት ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስ ቢሮ በክልሉ ከሚገኙ ዞኖች፣ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ ኦዲተሮች በኦዲት መሠረታዊ ፅንስ ሀሳብ ፣ኢንስፔክሽንና የውስጥ ኦዲት አፈጻጸም እንዲሁም የሂሳብ አያያዝና አስተዳደር ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ። የክልሉ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ የሺሀረግ ደበበ በስልጠናዉ መክፈቻ ላይ እንዳሉት፣ የኦዲት ስራ በቂ ዕውቀት ፣ክህሎት እና ልምድ መያዝን…
