Trendings

ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም ጉቦ የተቀበለ አመራርን ለህግ ማቅረቡን የክልሉ ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ገለጸ።

ህብረተሰቡ አገልግሎትን በምልጃና ጉቦ ለመፈፀም የሚፈልጉ አመራርና ሰራተኞች ላይ የተለመደውን ጥቆማ በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ኮሚሽኑ ጠይቋል። የክልሉ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሙስናና ብልሹ አሰራር መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ኮሚሽነር ዳግም ዳንኤል እንደተናገሩት ኮሚሽኑ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከህብረተሰቡ የሚደርሱ ጥቆማዎችን መሰረት በማድረግ የማጣራትና በህግ ስልጣን ለተሰጣቸው የፍትህ አካላት እያቀረቡ መሆኑን ገልጸዋል። ኮሚሽነር ዳግም…

Read More

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት ድሬዳዋ ገቡ ።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም ከፍተኛ የፌደራል ሚኒስትሮች በዛሬው እለት ድሬዳዋ የገቡ ሲሆን ድሬዳዋ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀርን ጨምሮ ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና…

Read More

የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ኤድዋርዶ ሮድሪጌዝ ፓሪላ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል።

Read More

ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመንገድ ደህንነት ፈንድ የቦርድ አባል ሆነው ተሾሙ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመንገድ ደህንነት ፈንድ የቦርድ አባል ሆነው ተሾመዋል፡፡ ኢትዮጵያ ሀገራዊ የመንገድ ደህንነት ስትራቴጂ በመቅረፅና የመንገድ ደህንነት ትምህርት በስርዓተ ትምህርት ውስጥ እንዲካተት በማድረግ የወሰደችው እርምጃ የመንገድ ደህንነትን ለማስፈን ያላትን ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑ ለሚኒስትሩ በተጻፈ ደብዳቤ ተገልጿል፡፡ በኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ስራዎች የተገነቡ ምቹ የብስክሌትና የእግረኛ መንገዶች እንዲሁም የተሻሻሉ የመንገድ…

Read More

የጤና መድኅንን ለማስቀጠል የፋይናንስ ዘላቂነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል ተባለ

የኢትዮጵያ የጤና መድኅን አገልግሎት ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ፣ ፍትህ ቢሮ፣ ከፋይናንስ ቢሮ እና ከዋና ኦዲት ቢሮ ከተውጣጡ ኃላፊዎች እና ጥሪ ከተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ጋር፣ የጤና መድኅንን ለማስቀጠል እና የፋይናንስ ዘላቂነትን ለማረጋገጥ በሚተገበሩ ተግባራት ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡ የኢትዮጵያ የጤና መድኅን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ወርቁ እንደገለጹት፣ የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድኅን ለማስቀጠል የፋይናንስ…

Read More

በቦንጋ ከተማ የመንገድ ዳር መብራት ሽቦ የሰረቀ ተከሳሽ እና የተሰረቀ ሽቦዎችን ከሌባ የገዛ አንድ ግለሰብ በእስራትና በገንዘብ መቀጣታቸዉን በካፋ ዞን ፍትህ መምሪያ አስታወቀ

ወንጀሉ የተፈጸመው በካፋ ዞን በቦንጋ ከተማ አስተዳደር ጥር 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከንጋቱ 12:00 ሰዓት በዩንቨርስቲ ቀጠና አበቺ መንደር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን ወንጀሉን የፈፀሙት ታረቀኝ ቆጭቶና ታምራት ወ/ማሪያም መሆናቸዉን የገለፁት በካፋ ዞን ፍትህ መምሪያ የታክስና ኢኮኖሚ ነክ ወንጀሎች ዐቃቤ ህግ አንዷአለም አሰፋ ናቸዉ። እንደ ዐቃቤ ህግ አንዷአለም ገለፃ ተከሳሽ ታረቀኝ ቆጭቶ የተባለው በተጠቀሰው ቀን…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የተፋሰስ ልማት ሥራን ጎበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የተፋሰስ ልማት ሥራን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ፣ የፌደራል እንዲሁም የክልሉ እና የዞኑ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

Read More

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኮሙኒኬሽን ዘዴ ልምድ በማካፈል ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገለጸ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኮሙኒኬሽን ዘዴ በልዩ አተያይ ሐሳቦችን፣ የሥራ ተነሳሽነትን የሚፈጥሩ ልምዶችንና ተግባራትን በማካፈል ላይ ያተኮረ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ገለጸ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልሎች የሚገኙ የሥራ ሪፖርቶችን ለሌሎች የተነሣሽነት ምንጭ እንዲሆኑ ሲያጋሩ መቆየታቸውንና ላለፉት ሰባት ዓመታት ለየት ባለ መንገድ ግልጽነትና ተደራሽነትን በማለም የኮሙኒኬሽን ስራው መከናወኑን ጽ/ቤቱ አስታውቋል፡፡ በዚህ ሂደት የክልሎች የሥራ ለውጦች…

Read More

ክልሉ ከተመሠረተ ወዲህ የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግራቸው እየተቀረፈ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተመሠረተ ወዲህ ዘመናትን ያስቆጠረ የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግራቸው መቀረፉን የዳውሮ ዞን ዛባ ጋዞ ወረዳ ደቼ ደነባ እና የካፋ ዞን ጠሎ ወረዳ ኦሚያ ቀበሌ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ክልሉ ከተደራጀ ወዲህ በዳዉሮ ዞን ዛባ ጋዞ ወረዳ ደቼ ደነባ ቀበሌ በ12 ሚሊዮን ብር ወጪ 2ሺህ 364 የቀበሌ ነዋሪዎችን እና የእንስሳት ውሃ ማጠጫ ገንዳዎችን ያካተተ…

Read More

የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ችግር እየገጠማቸው መሆኑን በሸካ ዞን የቴፒ ከተማ ና የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ

የሸካ ዞን ጤና መምሪያ የተገልጋዮች ቅሬታ እውነት መሆኑን አጣርቼ ለእርምት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል። ቅየህብረተሰብ ክፍሎችና ታካሚዎች እንደገለጹት ታክሞ ለመዳን እየመጣን በመፀዳጃ ቤት ጉድለት ላላስፈላጊ በሽታ እየተዳረጉ መሆኑን ገልጸዉ የባለሙያ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር፣የአልጋ ና የመድሀንት እጥረት እንዳለ ገልጸዋል። የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጂ አቶ ተገኝ ገቦ በበኩላቸው ሆስፒታሉ ከ2010 ዓ .ም ወዲህ ከመጀመሪያ ደረጃ ወደ አጠቃላይ ሆስፒታል ማደጉን…

Read More