የተጀማመሩ የልማትና የሠላም ግንባታ ተግባራት ከግብ እንዲደርስ ህዝቡ በጽናት ከመንግሥት ጎን መቆም አለበት – ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመትና የመጋቢት 24 ትሩፋቶችን የሚዘክር ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በቦንጋ ከተማ ላይ ተካሄደ። በድጋፍ ስልፉ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ ሀገራዊ ለውጡ በዘርፈ ብዙ ድሎች የታጀበ መኾኑን ተናግረዋል። መጋቢት 24 አካታችና ኅብረ-ብሄራዊ የፖለቲካ ስርዓት ግንባታ መሠረት የተጣለበት፣ ሀገራዊ ጠቀሜታ ያላቸው የህግ…
