በሚዛን አማን ከተማ ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሦስት ድልድዮች የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ
በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር በወንዞች ምክንያት ሲስተጓጎሉ የቆዩ የትራንስፖርት ችግሮችን ለመፍታት፣ ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነቡ የሦስት ድልድዮች የመሰረት ድንጋይ የመቀመጥ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል። በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን ባስተላለፉት መልዕክት፣ የብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት የህዝብን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን…
