የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክርቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።
በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ በተገባደደው 2016 በጀት ዓመት ምክር ቤቱ በህገ መንግስቱ የተሰጠዉን ሀላፊነት ለመወጣት በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። ከአቻ ክልሎች እንዲሁም ከተወካዮች ም/ቤትና ከፌደሬሽን ምክር ቤት ጋርም ተግባራትን በቅንጅት ማከናወን መቻሉን አፈጉባኤው ተናግረዋል። በ6ኛ ዙር 3ኛ የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ በም/ቤቱ በተቀመጡ አቅጫጫዎች ላይም በትኩረት…
