በግብርናው ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው ስኬት በማስቀጠል ከተረጂነት መላቀቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው – ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)
በግብርናው ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው ስኬት በማስቀጠል ከተረጂነት መላቀቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች ዘርፈ-ብዙ ጸጋዎች ያሏት ሀገር መሆኗን ተናግረዋል፡፡ እነዚህን ጸጋዎች በሚፈለገው ደረጃ ወደ ልማት መቀየር አለመቻላችን ደግሞ ከተረጅነት እንዳንወጣ አድርጎን ቆይቷል ነው ያሉት፡፡ አሁን ላይም ያሉንን ጸጋዎች በማልማት ከተረጂነት ወደ…
