ሁለተኛ ክልላዊ የትምህርት ጥራት ኮንፈረንስ በቦንጋ ከተማ መካሄድ ተጀመረ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች መምህራን ማህበር አዘጋጅነት ሁለተኛው ክልላዊ የትምህርት ጥራት ኮንፈረንስ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። የክልሉ መምህራን ማህበር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር በማድረግ እስከ ትምህርት ቤቶች ላይ በማውረድ ተግባራዊ እንዲደረግ እየተደረገ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አካሉ ዓለማየሁ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት እጅግ አሳሳቢ የሆነውን የትምህርት ጥራት ችግር ለመቅረፍ ማህበሩ…
