የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብ እና አለምአቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ባለፉት አራት ተከታታይ ቀናት በጅማ ከተማ ያዘጋጀው የ3ኛ ዙር የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል።
በስልጠናው የማጠቃለያ መድረክ በቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ መመሪያ የሰጡት የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ምክትል ሀላፊ ክቡር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ የብሔራዊነትን ትርክት አገራዊ አንድነትና ሕብረ ብሔራዊነትን በማስታረቅ ቅቡልነት ያለው አገረ መንግስት ግንባታ መፋጠን ወሳኝ አምድ በመሆኑ የሚዲያ የኮሚኒኬሽን ዘርፍ በትኩረት መስራት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ አሁን ባለንበት የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ የትርክት የበላይነት ለመውሰድ በፉክክር…
