Trendings

BLOGS

ባህላዊ ፍርድ ቤቶች ግጭቶችንና አለመግባባቶችን በእርቅ በመፍታት ፍትህን አስጠብቆ ለማየቆት የጎላ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ባህላዊ ፍርድ ቤቶቹን በአዋጅ ቁጥር 35/2016 መሠረት በማቋቋም በሁሉም ወረዳዎችና ቀበሌዎች አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ላይ ይገኛል። ለዚህም በክልሉ በምዕራብ ኦሞ ዞን በመኤኒት ጎልዲያ ወረዳ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ባህላዊ ፍርድ ቤቶቹ እስከ ቀበሌ ድረስ በማቋቋም ተግባራዊ በማድረግ ወደ ስራ ተገብቶ ውጤት ተመዝግቧል፡፡ በወረዳው ያነጋገርናቸው አንዳንድ ባህላዊ ፍርድ ቤት አካላት እንደገለጹት፣…

Read More

በጤናው ዘርፍ የተለዩ የገጠር ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎችን በመፈጸም የገጠሩን ማኅበረሰብ ኑሮ ማሻሻል ይገባል:- ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ የጤና ቢሮ “ዘላቂ እንቨስትመንት እና ፈጠራ ለጤናው ዘርፍ እምርታ” በሚል መርህ ቃል የጤና ሴክተር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥በጤናው ዘርፍ የተለዩ የገጠር ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎችን በመፈጸም የገጠሩን ማኅበረሰብ ኑሮ ማሻሻል ይገባል ብለዋል። የገጠር ትራንስፎርሜሽን፣ የገጠሩን ማኅበረሰብ አጠቃላይ ኑሮ ለማሻሻል ፈጠራና ፍጥነት እንዲሁም አንዳንድ ተግባራትን…

Read More

ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት የተላለፈ መልዕክት

የነፃ ምርት ዝውውርን ማስፈን የኢኮኖሚ ብልጽግናን የማረጋገጥ ጉዳይ ነዉ። የክልላችን ብልጽግና የሚረጋገጠው በሕግና በሥርዓት በተመራ ነፃ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ሲኖር ነዉ። በሀገራችን ነጻ የምርት ዝዉዉርን የሚገቱ በየአካባቢዉ የተቋቋሙ ኬላዎች እንዲነሱ መንግስት መወሰኑ ይታወቃል። መንግሥት የወሰነውን ይህንን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው ውሳኔ መሠረት በማድረግ፣ በየአካባቢው ተቋቁመው ነፃ የምርት ዝውውርን የሚያደናቅፉ ሕገ-ወጥ ኬላዎች ሁሉ እንዲነሱ መደረግ እንዳለበት ይታወቃል። ይህ…

Read More

በካፋ ዞን፣ጎባ ወረዳ የህዝብ የልማት ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ተግባራት እየተከናወነ መኾኑ ተገለጸ

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ ታደሰ ከክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ የህዝብ የልማት ተጠቃሚነትን የሚያሳድጉ በርካታ ተግባራት በወረዳው እየተከናወነ መኾኑን ተናግረዋል። ወረዳው፣ በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎች ሰፊ የልማት አቅም ያለው ወረዳ መኾኑን የጠቆሙት አቶ ታረቀኝ ለግብርናና ለቅመማ ቅመም ልማት ሰፊ አቅም ያለው እንደኾነ አስረድተዋል። ወረዳው በተለይም ለቡና ምርት ተስማሚ የአየር ፀባይና ስነምህዳር ያለው አከባቢ መኾኑን…

Read More

ህብረተሰቡ ራሱን ከወቅታዊ በሽታ ለመከላከል ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል።

ኅብረተሰቡ ከወቅታዊ ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለ የሄሞራጂክ ፊቨር በሽታ (Hemorrhagic Fever) ራሱን እንዲከላከል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ አሳስቧል። የቢሮው ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በመልዕክታቸው፥ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሽታ ለመጀመሪያ ጊዜ ከታየበት ከደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አከባቢ ጋር የሚዋሰን በመሆኑ ልዩ ጥንቃቄ ያሻል ብለዋል። በተለይም በክልሉ የምዕራብ ኦሞ ዞን እና የካፋ…

Read More

የህብረተሰቡን የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ትልቅ ሚና ያለው የሰንበት ገበያ በአመያ ከተማ ተጀመረ።

የህብረተሰቡን የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ትልቅ ሚና ያለው የሰንበት ገበያ በዛሬው በኮንታ ዞን አመያ ከተማ የዞኑን የከተማ አስተዳደር የመንግስትና የፓርቲ አመራሮች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል። በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የዞኑ ንግድና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ኡቴ እንደገለፁት በአመያ ከተማ አስተዳደር የኑሮ ውድነትን ለማቅለልና የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ትኩረት ተሰጥቶ እየሰራ መሆኑንና ለዚሁ ሥራ የሚያግዝ የሰንበት ገበያ…

Read More

የክልሉ የተቀናጀ አስተዳደር መረጃ ስርዓት (Integrated Management Information System) ዳታ ቤዝ መልማቱ ተገለፀ

በፌዴራል ስታትስክስ አገልግሎትና በአጋር የልማት ድርጅቶች /UNFPA/ ድጋፍ በክልሉ የመጀመሪያ የሆነው የለማ ክልላዊ ዳታ ቤዝ መሆኑ ተጠቁሟል። የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሰለሞን አየለ እንደገለፁ የክልሉን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ዲሞግራፊያዊ እንዲሁም የካርታ መረጃዎችን በማዘጋጀት በዳታ-ቤዝ በማደራጀት ለዕቅድ አውጪዎች፣ለውሳኔ ሰጭዎች፣ለፕሮጀክትና ፕሮግራም አዘጋጆች፣ለትምህርትና ምርምር ሥራዎች እንዲሁም ለኢኮኖሚ ዕድገቱ ዕገዛ የሚያደርጉ መረጃዎችን ማቅረብ ተቀዳሚ ተግባር መሆኑን…

Read More

በዳውሮ ዞን ጌና ወረዳ የኬሚካል ርጭት በማድረግ የወባን ጫና ለመቆጣጠር በከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነዉ

በጌና ወረዳ የወባ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሁሉም ቀበሌዎች ቤት ለቤት የወባ ኬሚካል ርጭት ዘመቻ በስፋት እየተካሄደ ነው። የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት እንዳስታወቀው፣ ይህ እርምጃ ከክልሉ መንግስት በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ጌና ወረዳ 100% የኬሚካል ርጭት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል። የወረዳው ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘነበ ዳማኮ ከኬሚካል ርጭቱ በተጨማሪ ሌሎች የተቀናጁ የመከላከያ መንገዶችም በስራ ላይ መሆናቸውን…

Read More

34ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ ዛሬ በአዳማ ከተማ ተጀመረ

”ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም” በሚል መሪ ቃል በተጀመረው ጉባዔ የ2017 የትምህርት ልማት ዘርፍ አፈጻጸም ይገመገማል። ‎ጉባዌው በ2018 የትምህርት ዘመን እቅድ ላይ ውይይት በማድረግ ለተሻለ አፈጻጸም የሚያግዙ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። ‎በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ በሚገኘው ሀገር አቀፍ ጉባዔ የኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ‎በተጨማሪም የህዝብ…

Read More