የተቀናጁ የምግብ ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋት እየተሰራ ነው
የተቀናጁ የምግብ ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋትና የምግብ ምርትን ለመጨመር እየተሰራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ገለጹ። ከትናንት ጥቅምት 26 እስከ 28 ቀን 2017 ዓ.ም እየተካሄደ የሚገኘው “ከረሃብ ነፃ ዓለም” ዓለም አቀፍ ጉባዔ በዛሬው ዕለትም ቀጥሏል። በጉባዔው የዛሬ ውሎ ኢንቨስትመንትን ማስፋፋትና የድኅረ-ምርት ብክነት ላይ ያተኮሩ የፓናል ውይይቶች ተካሂደዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ጠንካራ…
