የሌማት ትሩፋት ለግብርና ኢንቨስትመንትና ለሀገራዊ የስርዓተ ምግብ መሻሻል ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገለፀ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በደብረ ብርሃን ከተማ በሌማት ትሩፋት የተሰማራ የውጭ ባለሃብት የሥራ እንቅስቃሴን ተመልክተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ባቀድነው መሠረት በውጤታማነት እየተተገበረ ነው ብለዋል። የተመጣጠነ የምግብ ዋስትና ስርዓትን ለማረጋገጥ በሁሉም መስክ የተጀመሩ ሥራዎች የሚበረታቱ ናቸው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የደብረ-ሆላንድ የዶሮና እንቁላል ምርት ማዕከልም ሀገራዊ ውጥንን ለማሳካት የሚያግዝ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ማዕከሉ…
