የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢ ጉዳይ ቢሮ የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ምዕራፍ ሁለት ማስጀመሪያ አውደ ጥናት በቦንጋ ከተማ አካሂዷል።
አውደ ጥናቱ ላይ የተገኙት ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የ(LLRP )ፕሮጀክት በምዕራፍ አንድ ፕሮግራም በክልሉ የአርብቶ አደር አካባቢዎች ላይ ከትምህርት ቁሳቁስ አንስቶ እሰከ መሰረተ ልማት በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን ገልፀው ለ5 ወረዳዎች ለተከታታይ አምስት ዓመታት የሚውል 17 ሚለዮን 136 ሺ 666.70 ዶላር ለፕሮጀክቱ ማሳኪያ መመደቡን ተናግረዋል። ይህ ትልቅ በጀት የተመደበለት ፕሮጀክት በውጤት…
