Trendings

የግብርና ምርትና ምርታማነትን በመጨመር የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል- ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብር ቢሮ በምግበ ስረዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ትብብር በካፋ ዞን፣ አዲዮ ወረዳ በኖራ የታከመ የመኸር ስንዴ ማሳ የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል። በክልሉ የግብርና ምርትና ምርታማነትን በመጨመር የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ በአርሶአደሩ ማሳና በማሰልጠኛ ተቋማት በምርምር በመታገዝ እና የተሞላ ግብዓትን በመጠቀም የተጀመረው ተግባር አበረታች ውጤት እያሳየ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ነው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር…

Read More

የህዝብ ተጠቃሚነት በሁሉም ዘርፍ እንዲረጋገጥ ተቋማት የህዝብ ውክልና ስራዎችን በተገቢው ሊወጡ ይገባል ፦ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ጸሀይ ዳርጫ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የአስፈጻሚ ተቋማት ዕቅድ አፈጻጸም በቦንጋ ከተማ እየገመገመ ነው። የህግ፤ ፍትህና መልካም አስተዳደር ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ፤ማህበራዊ ጉዳዮች ዘርፍ ፤ግብርና እና ገጠር ልማት፤ከተማና መሠረተ ልማት ዘርፍ ፤እንዲሁም በጀት፤ ፋይናንስና ኦዲት ጉዳዮች ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች ናቸው አፈጻጸሙን እየገመገሙ የሚገኙት። የክልሉ ምክር ቤት…

Read More

በ19ኛው የብሔረሰቦች ቀን በዓል የክልሉ ቱባ ባህልና መልካም እሴቶች ጎልተው እንዲወጡ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መቱ አኩ የበዓሉን አከባበር ቅደመ ዝግጅት ስራዎችን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል። የክልሉ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መቱ አኩ እንደገለፁት 19ኛው በሀገር አቀፍ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ የብሔረሰቦች ህዝቦች ቀን በዓልን አስመልክቶ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ሀገራዊ መሪ ቃሉ ላይ በቂ ግንዛቤ በመያዝ…

Read More

የገቢ ግብርን ከማሰባሰብ ባሻገር በዘርፉ የሚታየውን ህገ ወጥ አሠራርና ማጭበርበርን በመግታት የህግ ተጠያቂነት ማስፈን በቀጣይ ልዩ ትኩረት እንደሚሻ ተገለጸ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ገቢዎች ቢሮ በግብር ህግ ማስከበር ዘርፍ የግብር ህግ ማስከበር ዳይረክቶሬት ለታክስ መረጃ አደራጅ፣ ለታክስ ህግ ተገዥነትና የስጋት ስራ አመራር ባለሙያዎች በቦንጋ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል ። የቢሮ ምክትል ኃላፊና የግብር ህግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት በላይ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የዘርፉ ባለሙያዎች ለዘርፉ ስራ ልዩ ትኩረት በመስጠት በግብር አሰባሰብ ላይ የሚታዩ…

Read More

የህገመንግሰት እና ለፌራልዝም አስተሳሰብ እንዲጎለብት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል፦ አቶ መቱ አኩ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት 19ኛው የኢትዮጵያ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ ህብረ ብሔራዊ የፌዴራልዝም ሥርዓት በኢትዮጵያ፣ ተግዳሮቶችና የመፍትሔ ሀሳቦች ላይ ለባለድርሻ አካላት በቦንጋ ከተማ ስልጠና ተሰጥቷል። የክልሉ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ መቱ አኩ በስልጠናው መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የስልጠናው ዋና ዓላማ ህብረ ብሔራዊ ፌዴራልዝም ሥርዓት…

Read More

የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ውጤታማ ለመሆን የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መስራት እንደሚገባቸው ተገለፀ

የቤንች ሸኮ ዞን ሥራ ክህሎት ኢንተርፕራይዝ ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ የ2017 የ4 ወራት ተግባር አፈፃፀም ግምገማና የክህሎት መር የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው። የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት እንደ ሀገር ከአለንበት ድህነት ሊያወጣ የሚችለውን የክህሎት መር እንዲሆን ፖሊሲና ስትራቴጂ ወጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በክህሎት መር ለወጣቶች ስራ ዕድል በመፍጠር ተጠቃሚ ከማድረግ…

Read More

በክልሉ ለ3ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረው የብሔረሰቦች ቀን በዓል በድምቀት እንዲከበር ሰፊ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች መከናወናቸው ተገለጸ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለ3ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረው የብሔረሰቦች ቀን በዓል በድምቀት እንዲከበር ሰፊ ስራዎች መከናወናቸው ተገልጿል። ለበዓሉ ድምቀት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅቶች በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን የገለፁ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ በዓሉ በክልሉ ሁሉም አከባቢዎች ከቀበሌ ጀምሮ በትምህርት ቤቶችና በተለያዩ ቦታዎች በድምቀት እየተከበረ መቆየቱን…

Read More

“የወባ በሽታ የመከላከሉ ተግባር አሁንም በተለየ ትኩረት ህብረተሰባችንን በማሳተፍ መተግበር አለበት” የክልሉ ጤና ቢሮ

በኢትዮጵያ የክረምቱን መውጣት ተከትሎ ከሚከሰቱ በሽታዎች ወባ በሽታ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል፡፡ በተለይም ከመስከረም እስከ ታህሳስ ባሉት ወራቶች የወባ በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጭበት ወቅት ነው። በሃገራችን ኢትዮጵያ የወባ በሽታ ስርጭትን ለመቀነስ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ሲሆን ከባለፈው አመት ጀምሮ ግን በሽታው በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች የመስፋፋት አዝማሚያ እያሳየ መጥቷል፡፡ ከመላ አገሪቱ 75 በመቶ የሚሆኑት አካባቢዎች ለወባ በሽታ ስርጭት…

Read More

የማህፀን በር ካንሰር የመከላከያ ክትባት ዘመቻ በይፋ ተጀመረ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የማህፀን በር ካንሰር የመከላከያ ክትባት ዘመቻ በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ በይፋ ተጀምሯል። ዘመቻውን በይፋ ያስጀመሩ የክልሉ ጤና ቢሮ ጤናና ጤና ነክ ግብአት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርና የቢሮው ተወካይ አቶ ሙሉቀን አሰፋ ወላጆችና አሳዳጊዎች እድሜአቸው ከ9 – 14 የሆኑ ልጃገረዶችን በማስከተብ ከማህፀን በር ካንሰር መከላከል ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። በክልሉ ከ157 ሺ…

Read More