የአሰራር መመሪያዎችን ባልተከተለ መንገድ የሚፈጸሙ ተግባራት የኦዲት ግኝቶች ላይ የሚወሰደው የእርምት እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት አስታወቀ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ዋና ኦዲት መ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት የኦዲት አፈጻጸሙን ለክልሉ ም/ቤት አቅርቧል ። የዋናው ኦዲት መስሪያቤት የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት ዋና ኦዲተር አቶ አስራት አበበ በበጀት ዓመቱ በፋይናንሻልና ህጋዊነት፣ 1ኛ ዙር ኢንቲሪም ኦዲት፣የክልሉ የተጠቃለለ ገቢና ወጪ ኦዲት፣የክዋኔና አካባቢ ጥበቃ ኦዲት ጭብጦች፣በልዩ ኦዲት፣በገቢና የንብረት ኦዲቶች ላይ ትኩረት በማድረግ መሰራቱን አብራርተዋል ። በክዋኔ…
