እየጣለ ያለውን ከፍተኛ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት የተዘጋውን መንገድ ጊዜያዊ ጥገና እያደረ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ገለጸ
በቤንች ሸኮ ዞን ከዋቻ ማጂ ወደ ሼይቤንች የሚወስደው መንገድ በመዘጋቱ በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ጫና እያሳደረ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል ፡፡ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የክረምቱን ዝናብ ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች የመሬት መንሸራተቶች እየተከሰቱ ይገኛሉ ፡፡ በክልሉ ቤንች ሸኮ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ ቃሻ ቀበሌ ላይ የተከሰተው የመሬት መንሸራተት ዜጎች እንዲፈናቀሉ ከማድረጉም በላይ በቤንች ሸኮና በምዕራብ ኦሞ…
