በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብሔረሰቦችን የጋራ ዕሴት ማጎልበት የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ ሲል የክልሉ ብሄረሰቦች ምክር ቤት ገለፀ
የብሔረሰቦች ምክር ቤት የክልሉን ህገ መንግስት የመተርጎም፣ አጣሪ ጉባኤ የማደራጀት እንዲሁም በክልሉ ዉስጥ የሚነሱ ችግሮችን መፍትሔ የማፈላለግ እና የህዝቦችን ባህልና ታሪክ የማጠናከር ስልጣን አለው፡፡ በክልሉ ከሚገኙ ከ13 ነባር ብሔር/ብሔረሰቦች የተወከሉ 70 አባላትን ያቀፈዉ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት እያንዳንዱ ብሔር/ብሔረሰብ አምስት ተወካዮች ሲኖሩት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ባለበት ተጨማሪ አምስት ተወካዮች የሚኖሩት በመሆኑ በዚህም መሠረት የካፋ…
