በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በዩኒሴፍ ፕሮግራም ገንዘብ ድጋፍ በተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ አፈጻጸም ተመዝግቧል፦ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የዩኒሰፍ ፕሮግራም አፈጻጸም በቦንጋ ከተማ ገምግሟል። በክልሉ ዩኒሴፍ ፕሮግራም ገንዘብ ድጋፍ በስምንት ቢሮዎች እና በ17 ወረዳዎች የተለያዩ ፕሮግራሞች እየተከናወነ ይገኛል። የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ በወቅቱ እንደገለጹት በ2016 በጀት ዓመት በክልሉ በዩኒሴፍ ፕሮግራም ገንዘብ ድጋፍ በስምንት ቢሮዎችና በ17 ወረዳዎች…
