የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ በታርጫ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
በጉባኤው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የመንግስታቸውን የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የማህበራዊ ዘርፍ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለክልሉ ምክር ቤት እያቀረቡ ይገኛሉ። ባለፉት ስድስት በትምህርት ዘርፍ ”ትምህርት ለትውልድ ኢንሼቲቭ” 372 ሚሊዮን 4መቶ 75 ሺህ በላይ ብር በመሰብሰብ 489 መማሪያ ክፍሎች ግንባታ፤ 1,385 መማሪያ ክፍሎች ጥገና ሥራ ማከናወን ተችሏል። በክልል ደረጃ በልዩ ንቅናቄ 60…
