Trendings

የብሔረሰቡ ቋንቋና ታሪክ ላይ በደንብ ለመስራት የተቀናጀና ቀጣይነት ያለውን ሥራ እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ

የማጃንግ ብሔረሰብ የቋንቋና ባህል ሲምፖዚየም የብሔረሰቡ ተወላጆችና ወዳጆች በተገኙበት በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ፓናል ውይይት አካኺዷል ። የፓናል ውይይቱን መነሻ ነጥቦች የሚጠቁም ሰነድ ያቀረቡት የደቡብ ምዕራብ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት ጸ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ እንዳሻው: ብሔረሰቡ ከጥንት ጀምሮ የራሱ የሆነ ባህላዊ ክዋኔ፣ ቋንቋ፣ ወቅትና ወራት አቆጣጠር ያለው ህዝብ መሆኑን አሳይተዋል። በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ አያያዝ እስከ…

Read More

በሚዛን አማን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መከፈቱ የአካባቢውን ማህበረሰብ የሚያወጣውን ገንዘብና የሚያባክነውን ጊዜ እንደሚቆጥብ ተገለፀ።

​በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የሚዛን አማን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መከፈቱ፣ አገልግሎት ፈላጊዎችን ለከፍተኛ እንግልትና ወጪ ሲዳርግ የነበረውን ጉዞ እንደሚያስቀር የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ጀማል ደስታው ገለጹ። ​ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ መደበኛ አገልግሎቶችን መስጠት መጀመሩን አቶ ጀማል ጠቁመው ዜጎች የፓስፖርትና ሌሎች ተያያዥ አገልግሎቶችን በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ ለማድረግ ተቋሙ በሰፊው እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ​እንደ አቶ ጀማል ገለጻ፣ ተቋሙ ሀገራዊና…

Read More

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሌሴቶና ሞሮኮ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሌሴቶ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌጆን ምፖትጆአኔ እና ከሞሮኮ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናስር ቡሪታ ጋር ተወያይተዋል፡፡ ጌዲዮን (ዶ/ር) ከሌሴቶ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌጆን ምፖትጆአኔ ጋር ባደረጉት ውይይት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ውጤታማ በሆነችባቸው ዘርፎች ለሌሴቶ ልምዷን ለማካፈል ዝግጁ እንደሆነች መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡…

Read More

የክልሉ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 47ኛ መደበኛ ስብሰባዉን በሃለላ ኬላ አካሂዷል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት መስተዳድ ምክር ቤት ዛሬ በሃላላ ኬላ ባካሄደዉ 47ኛዉ መደበኛ ስብሰባ በ1ኛ አጀንዳነት የተመለከተዉ የክልሉ መንግስት የአስፈጻሚ ተቋማት የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈጻጸም ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ በመሉ ድምጽ አጽድቋል። ምክር ቤቱ በ2ኛ አጀንዳነት የመንግስት ፍርድ ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት ለመወሰን የወጣ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አስተያየት በመስጠት ወደ ምክር…

Read More

የማጃንግ ብሔረሰብ ውብ ባህል ያለውና ከሌሎች ህዝብ ጋር አብሮ የመኖር የዳበረ ልምድ ያለዉ ህዝብ ነው:- አቶ አበበ ማሞ

የማጃንግ ብሔረሰብ የቋንቋና ባህል ሲምፖዚየም የብሔረሰቡ ተወላጆችና ወዳጆች በተገኙበት በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በፓናል ውይይት ተጀምሯል ። የብሔረሰቡን ቀደምት እሴቶችን ለማነቃቃትና ለማልማት ያለመው የመጀመሪያውና ታሪካዊው የየቋንቋና ባህል ሲምፖዚየም: ቱባ ባህሉ ይዘቱን ጠብቀው ለቀጣዩ ትውልድና ለዓለም ለማስተዋወቅ መሠረት የሚጣልበት ታላቅ ቀን መሆኑ ተመላክተዋል። በሲምፖዚየሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ የለውጡ…

Read More

48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። በስብሰባው የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ፣ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስን (ዶ/ር) ጨምሮ የሕብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች፣ የሕብረቱ ተቋማት አመራሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ ዛሬና ነገ ለሁለት…

Read More

የክልሉ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 47ኛ መደበኛ ስብሰባዉን በሃለላ ኬላ እያካሄደ ይገኛል ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት መስተዳድ ምክር ቤት ዛሬ በሃላላ ኬላ 47ኛዉ መደበኛ ስብሰባ እያካሄደ ነዉ። መስተዳድር ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባዉ የክልሉን መንግስት አስፈጻሚ ተቋማት የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈጻጸም የሚገመገም ሲሆን ሌሎች አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።

Read More

“የውኒ ወንዝ ሰው ከመብላት፣ ሰው ወደ ማብላት ተሸጋግሯል” – የገንዶ ነዋሪዎች

በኢትዮጵያ የስንዴ ልማትን “በመስኖ ላይ የተመሰረተ የስንዴ ምርት ከውጭ ከመቀበል ወደ ውጭ ለመላክ የሚደረግ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የመስኖ ስንዴ ልማት ሥራ ውጤታማ እየኾነ እንደሚገኝ ከግብርና ሚኒስትር የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በክልላችን ተጨባጭ፣ በክልሉ ምሥረታ ወቅት የመስኖ አውታር ከነበረበት አነስተኛ ሽፋን አሁን ላይ የክልሉ መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት ትርጉም ባለው መልኩ መሻሻል አሳይቷል። ምንም…

Read More

የማጃንግ ብሔረሰብ የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየምለማካሄድ ዝግጅቱ ተጠናቋል። ኮሚቴዉ

የማጃንግ ብሔረሰብን የቀደሙ የባህል እሴቶችና ቋንቋ ለማነቃቃት እና ለልማት ለማዋል ያለመ ታላቅ የባህልና የቋንቋ ሲምፖዚየም የካቲት 4 እና 5 በቴፒ ከተማ እንደሚካሄድ የዝግጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሐንስ በንዲ ገለጹ። አቶ ዮሐንስ እንደገለጹት፣ ለሲምፖዚየሙ የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በሙሉ ተጠናቀዋል። የሲምፖዚየሙ ዋና ዓላማ ለረዥም ጊዜ ተዘንግተው የነበሩ የማጃንግ ብሔረሰብ ባህላዊ እሴቶችንና የአኗኗር ዘይቤዎችን እንደገና ማንቃት…

Read More

ከ11ሺህ በላይ ማኅበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመረቀ።

በዳውሮ ዞን ከጪ ወረዳ፣ የከጪ ከተማ የንጹሕ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በገተገኙበት ተመርቋል። በክልሉ መንግሥት የበጀት ድጋፍ የተገነባው የከጪ ከተማ ንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በተገኙበት ተመርቀው ለአግልግሎት ክፍት ሆኗል። ፕሮጀክቱ በከጪ ከተማ ለረጅም ጊዜ ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግርና የህዝብ ጥያቄ ሆኖ የቆየውን…

Read More