በክልሉ ያለውን ሰላምና ፀጥታ በዘላቂነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ስራዎችን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ ተናገሩ
ርዕሰ መስተዳድሩ በምዕራብ ኦሞ ዞን ስላለው ወቅታዊ የሠላምና ፀጥታ ጉዳይ ላይ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ጋር የውይይት መድረክ በሚዛን አማን ከተማ አካሂደዋል። በመድረኩ ላይ በምዕራብ ኦሞ ዞን ከሚገኙ ከአራት ወረዳዎች የተውጣጡ አመራሮችና የሀገር ሽማግሌዎች ተሳትፈዋል። በምዕራብ ኦሞ ዞን የአርብቶ አደር አካባቢዎች አልፎ አልፎ የሚከሰተውን የእርስ በርስ ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት በየደረጃው የሚገኙ አካላት በቅንጅት መስራት አለባቸው ብለዋል።…
