Trendings

መንግስት በትምህርት ጥራት ላይ እያደረገ ላለው ሪፎርም የቅድመ መደበኛ ትምህርት ፕሮግራም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ

በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት እስታንዳርዱን አሟልተው ወደ ትግበራ መግባቱን መመልከት ተችለዋል። የለውጡ መንግስት በትምህርት ሴክተር ላይ ይዘው ከመጣባቸው ኢኒሼቲቮች ቀዳሚው ቅድመ አንደኛ ትምህርት ነው ያሉት የአዲስ ፋና አንደኛ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አበበ ቢቂላ: የትምህርት ጥራት ችግርን ከስሩ ለማከም አይነተኛ ሚና እንዳለው ገልፀዋል። የቅድመ መደበኛ ትምህርት በእስታንዳርዱ መሠረት…

Read More

ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ለሶስተኛ ጊዜ ያሰለጠናቸዉ የመካከለኛ እና ከፍተኛ ማዕረግ ሽግግር ሰልጣኞችን እያስመረቀ ነዉ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም ለሶስተኛ ጊዜ ያሰለጠናቸው የመካከለኛ እና ከፍተኛ ማዕረግ ሽግግር ሰልጣኝ የፖሊስ መኮንኖችን እያስመረቀ ይገኛል። ሰልጠኞቹ የቆይታ ጊዜያቸዉን የሸፈኑ ከዋና ሳጅን ወደ ረዳት ኢንስፔክተር እና ከኢንስፔክተር ወደ ዋና ኢንስፔክተር ሽግግር የሚያደርጉ ሲሆኑ የፖሊስ አመራርነት አቅም ግንባታ ስልጠና የወሰዱ ናቸዉ።…

Read More

ተቋማዊ አሰራር በማጠናከር የተጀመረውን የትምህርት ልማት ሥራ ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የግማሽ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የድጋፍና ክትትል ግብረ-መልስ መድረክ በቦንጋ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የአፈጻጸም ሪፖርት እና ቢሮው በ156 ትምህርት ቤቶች ያደረገው የድጋፍና ክትትል ግብረ-መልስ ሪፓርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል በአደረጃጀት እየተሰራ ያለውን ሁሉን አቀፍ ተግባር ወጥነት ባለው መልኩ በሁሉም የክልሉ አከባቢ ማስቀጠል…

Read More

የከንቲባ ችሎት የህዝብ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመፍታት ዓይነተኛ ሚና እንዳለው ተገለጸ።

የአውራዳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ችሎት የህዝብ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ ። የለውጡ መንግስት የህዝብን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በከተማችን የከንቲባ ችሎት በ2017 ዓ/ም ስራ መጀመሩን የአውራዳ ከተማ ከንቲባ አቶ ታረቀኝ ኃይሌ ተናግረዋል። የከንቲባ ችሎት የከተማ መሬት አገልግሎት አሰጣጥ፣ የፍትህ እጦት፣የመልካም አስተዳደር ችግር፣የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ እና ሌሎች…

Read More

በክልሉ የሚገኙ የመስኖ ተቋማት የግብርና ምርትና ምርታማነት ማሳደግ ላይ ትኩረት በማድረግ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በአመያ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የተገኙት የክልሉ የመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ፋልታሞ ድብሎ በሀገሪቱ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ የተጀመረውን መፍጠር፣ መፍጠንና መዝለል መርህን በመከተል እየተሰራ ያለውን ስራ ለማስፈፀም እንደተቋም የተሰጡ ተልዕኮዎችን በተገቢው…

Read More

የክልሉ የድጋፍና ክትትል ቡድን በካፋ ዞን ወቅታዊ የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎችን ስያካሂድ የነበረውን አፈጻጸም እየገመገመ ይገኛል።

ግምገማው በዋናነት በመደበኛ በፓርቲ ስራዎችና በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ የተቀመጡ ሀገራዊ 6ቱ የትኩረት አቅጣጫ ግቦችን ስኬታማ ለማድረግ በዞኑ እየተሰራ ያለው አፈጻጸም በጥንካሬና በጉድለት በመገምገም ተግባራቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ ሰሌዳ ስኬታማ ለማድረግ ታሳብ ያደረገ ነው። ለግምገማ መድረኩ የተዘጋጀውን የዞኑን ወቅታዊ አፈጻጸም ሪፖርት የካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ታከለ ታምሩ እያቀረቡ ይገኛል…

Read More

በክልሉ በተለያዩ ምክንያቶች ከትምህርት ገበታ የቀሩ ህጻናት የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው – ደስታ ገነሜ (ዶ/ር)

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ በተለያዩ ምክንያቶች ከትምህርት ገበታ የቀሩ ህጻናትን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ “የተፋጠነ ትምህርት መርሐ ግብር” ስልጠና በቦንጋ እና በታርጫ ከተሞች እየሰጠ ይገኛል። በክልሉ በተለያዩ ምክንያቶች የትምህርት ዕድል ያላገኙ ህጻናትን ወደ ትምህርት ቤት ለማስገባትና የትምህርት ተሳትፎ ለማጎልበት እየተሰራ እንደሚገኝ ነው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትልና የመማር ማስተማር ዘርፍ ሀላፊ ደስታ ገነሜ (ዶ/ር)…

Read More

ህብረተሰቡ የመድኃኒት አጠቃቀም ሥርዓትን በማሻሻል መድኃኒት ከተላመዱ በሽታዎች ራሱን እንዲጠብቅ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ

ዓለም አቀፍ የፀረ-ተዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት”አሁን እንተግብር፣ ዛሬን እንጠብቅ፣ የወደፊታችንን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል በቦንጋ ከተማ እየተካኸደ ነው። በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሒም ተማም ዓለም አቀፍ የፀረ-ተዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ የጤና ስጋት እየሆነ ስለመጣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄው በተቀናጀ መልኩ ወደ ህብረተሰቡ መድረስ…

Read More

ኡሲቃ የተፈጥሮ ፍል ውሃ

ኡሱቃ የተፈጥሮ ፍል ውሃ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ ዞን በሸኮ ወረዳ ሺሚ ቀበሌ ኡሱቃ መንደር ይገኛል። ፍል ውሃው በአረንጓዴና ውብ በሆነው ደን የተከበበ ሲሆን ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በመምጣት በርካታ ሰዎች እንደሚጎበኙም ተጠቁሟል። የተፈጥሮ ፍል ውሃው በቁጥር 44 ምንጭ ያለውና ለተለያዩ በሽታዎች እንደ ፈውስ ያገለግላል። በየዓመቱ ከተለያዩ አከባቢዎች የሚመጡ ሰዎች ከማስጎብኘት ባለፈ የተፈጥሮ…

Read More

በክልሉ የትምህርት ጥራትን ከመሠረቱ ለማረጋገጥ በተሰጠው ትኩረት አበረታች ውጤት ተመዝግቧል – አቶ አልማው ዘውዴ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የግማሽ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የድጋፍና ክትትል ግብረ-መልስ መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት የትምህርት ጥራት በማሻሻል በሁሉም ደረጃ የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል መጠነ ሰፊ ተግባራት መከናወኑን ነው በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የቢሮው ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ በመክፈቻ ንግግራቸው የጠቆሙት።…

Read More