በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ልማት የግሉን ዘርፍ በስፋት እንዲሳተፍ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ
የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን አገር አቀፍ የንግድ ሳምንት ኤግዚቢሽንን ምክንያት በማድረግ “አረንጓዴ ኢኮኖሚን እውን በማደረግ ሂደት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሚና “በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት አካሂዷል። ከውይይቱ ጎን ለጎንም በኃይል ቁጠባ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡና፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሽያጭ የፈጸሙ ኩባንያዎችና ድርጅቶች እውቅና ተሰጥቷል። በሥነ-ስርዓቱ ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶክተር)፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሰሃረላ…
