በበጀት ዓመቱ የገጠር የጤና ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች በተሟላ መልኩ መፈጸም እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ የጤና ቢሮ “ዘላቂ እንቨስትመንት እና ፈጠራ ለጤናው ዘርፍ እምርታ” በሚል መርህ ቃል ያዘጋጀው የጤና ሴክተር ጉባኤ በታርጫ ከተማ ተካሂዷል። ለጤናው ዘርፍ ውጤታማነት ብቃት ያለውን የአመራር ስርዓት መፈጠር እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገልጸዋል። የጤናውን ዘርፍ ተልዕኮ በተሻለ መልኩ ለማሳካት የዘርፉ አመራር የተግባር ቁርጠኝነት መጠናከር እንዳለበት ያነሱት ርዕሰ…
