Trendings

በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን ለማስፋት ለቴክኖሎጂ እና አዳዲስ አሰራሮች ትኩረት ተደርጓል – ዶክተር አየለ ተሾመ::

በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎትን ጥራትና ተደራሽነት ለማስፋት ቴክኖሎጂ እና አዳዲስ አሰራሮችን ማጠናከር ላይ ትኩረት መደረጉን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ ተናገሩ። ሚኒስትር ዴኤታው ይህን ያሉት በአፍሪካ ህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ በሚገኘው ስምንተኛው ሀገር አቀፍ የጤና ኢኖቬሽንና ጥራት ጉባኤ ላይ ነው። ዶክተር አየለ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ በጤና ኤክስቴንሽን፣ በወረዳ ሽግግር እና አጠቃላይ የለውጥ ስራዎች ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል።…

Read More

የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደቱ ግለፀኝነትና አሳታፊ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ገለፁ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እየተከናወነ ያለውን 3ኛ ቀኑን የያዘውን የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ አስመልክቶ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቦንጋ ከተማ መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫው ላይ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ የእስካሁን ያለውን የምክክሩን ሂደት ከሁሉም ወረዳዎች የተመረጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ወኪሎች ግልጽና አሳታፊ በሆነ መልኩ አጀንዳቸውን አደራጅተው ያጠናቀቁበት የምክክር መድረክ መሆኑን ገልፀዋል። በክልሉ የህብረተሰብ ወኪሎች…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት ስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል ፡፡

በጉባኤው ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ለምክር ቤቱ የ2017 በጀት ዓ/ም ዕቅድ አፈጻጸም ማቅረብ ጀምረዋል ፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት የአፈጻጸም ሪፖርት ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ፡- በበጀት ዓመቱ በክልሉ የሚገኙ የተፈጥሮ ጸጋዎችንና የልማት ኃይሎችን በመጠቀም ፈጣንና ቀጣይነት ያለዉ ሁለንተናዊ እድገት ማስመዝገብ የሚያስችሉ ክልላዊ ስራዎች ተከናወነዋል ፡፡ በአብዛኛው ዘርፎች ካለፉት ዓመታት የተሻለ ውጤት…

Read More

በቦስተን የኒው ባላንስ የቤት ውስጥ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይና ለሜቻ ግርማ አሸነፉ::

በቦስተን የኒው ባላንስ የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይ እና ለሜቻ ግርማ ውድድሩን በበላይነት አጠናቅቀዋል፡፡ በ1 ሺህ 500 ሜትር የተወዳደረችው ጉዳፍ ፀጋይ ርቀቱን በ3 ደቂቃ 58 ሰከንድ ከ11 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆናለች፡፡ በዚሁ ርቀት የ18 ዓመቷ አትሌት ብርቄ ሀየሎም 3 ደቂቃ 58 ሰከንድ ከ43 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡ ወጣቷ…

Read More

የአማራ ክልል አሁናዊ ሁኔታን በተመለከተ

በአማራ ክልል ላይ ከየትኛውም መንግስት በላይ አሁን ያለው መንግስት በርካታ የልማት ስራዎችን እያከናወነ ነው፡፡ በክልሉ ታላላቅ የመንገድ፣ የኢንዱስትሪ የቱሪዝም ልማቶች እየተከናወኑ ነው፡፡ በዚህም ክልሉን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡ የፋሲል ቤተ-መንግስት እየታደሰ ነው፤ በዋና ዋና ከተሞች የኮሪደር ልማት እየተከናወነ ነው፡፡ የመገጭ ግድብን 7 ቢሊዩን ብር መድበን ከበርካታ ዓመታት የግንባታ መቋረጥ በኋላ ቀን ከሌት እየገነባን ነው፡፡…

Read More

ህንግጫ ህዝባዊ መሠረት ይዞ እንዲከበርና በሚፈለገው ልክ እንዲያድግ ሁሉም የብሔረሰቡ ተወላጆችና ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ ይገባል

ህንግጫ ህዝባዊ መሠረት ይዞ እንዲከበርና በሚፈለገው ልክ እንዲያድግ ሁሉም የብሔረሰቡ ተወላጆችና ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ ይገባል፦አቶ ታከለ ተስፉ የኮንታ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ህንግጫ’በዓል ዕርቀ- ሰላም የሚወርድበት፣የተራራቁት የሚሰበሰቡት ፣ጎዶሎዉ ሞልቶ በሙላት የመሻገር አስተምሮ፣ የአብሮነት እና የአንድነት መገለጫ ነዉ ሲሉ የኮንታ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ ታከለ ተስፉ ገለጹ። የኮንታ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ የ”ህንግጫ” በዓል አካል የሆነዉ የባህልና…

Read More

ኢትዮጵያ እና ማሌዢያ ከዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው ባሻገር

ኢትዮጵያ በደቡብ ምስራቅ እስያ ከምትገኘውና የቅይጥ ኢኮኖሚ ባለቤት ከሆነችው ማሌዢያ ጋር ዲፕሎማሲያ ግንኙነቷን የጀመረችው በአውሮፓውያኑ 2003 ነው። በዚሁ አመት ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ዋና ከተማ ኳላላምፑር ቆንፅላ ጽሕፈት ቤቷን በመክፈት የሁለትዮሽ ግንኙነቱን በዲፕሎማሲ አጠናክረዋለች። ቆንፅላ ጽሕፈት ቤቱም በሀገራቱ መካከል ያለውን የንግድና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማሳደግ ስራዎችን በመስራቱ ብዙ የማሌዢያ ኩባንያዎች በእርሻና በማዕድን ዘርፍ ተሰማርተው ይገኛሉ። ማሌዢያ ቅይጥ ኢኮኖሚ…

Read More

በ118 ሚለየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የሰንገጢ- ጩርጩራ የመንገድ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

በዳውሮ ዞን ኢሳራ ወረዳ የተገነባውን የሰንገጢ -ጩርጩራ የመንገድ ፕሮጀክትተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል። 40 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው በዳውሮ ዞን ኢሳራ ወረዳ የተገነባውን የሰንገጢ ጩርጩራ መንገድ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) መርቀው ከፍተዋል። መንገዱ የተገነባው ከክልሉ መንግስት በተመደበው 83 ሚለየን ብር እና የዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈፀሚያ በተመደበው 35 ሚለየን…

Read More

ምክክር ለጋራ አሸናፊነት፣ ምክክር ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረመንግሥት ግንባታ – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

በኢትዮጵያ ለዘመናት ያለመግባባትና የንትርክ እንዲሁም የእርስ በርስ ግጭት ምንጭ የነበረው ኋላቀር የፖለቲካ ባህላችን የወለደው ችግር ነው። ይህን ችግር በመሠረታዊነት ለመቅረፍ እና በሀገራዊ ጉዳዮችና በብሔራዊ አጀንዳዎች ዙርያ የሚታዩ ልዩነቶችንና መካረሮችን ለማረቅ ሀገራዊ ምክክር ወሳኝ ጉዳይ ነው ፡፡ መንግሥት አዎንታዊ የሰላም ባህል እንዲሰፍንና የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል ተገንብቶ ኢትየጵያውያን ችግሮቻቸውን በጠረጴዛ ዙርያ በሃሳብ አውድ ብቻ መፍታት አለባቸው የሚል…

Read More

የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ለውጥ በማረጋገጥ የአድዋ ድልን ማጽናት እንደሚገባ ተገለጸ

129ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል!” በሚል መርህ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቦንጋ ከተማ በድምቀት ተከብሯል። በዓሉን በሚመለከት በቀረበው ፓናል ውይይት ሀሳብ የሰጡት የክብረ በዓሉ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ለውጥ በማረጋገጥ የአድዋ ድልን በትውልድ ውስጥ ማጽናት እንደሚገባ ተናግረዋል። አድዋ የመደማመጥና የመከባበር እንዲሁም በአንድነት የመቆም ውጤት መሆኑን የጠቆሙት የመድረኩ ተሳታፊዎች የአሁኑ ትውልድ፥…

Read More