Trendings

በግብርናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለይቶ በመፍታት ምርትና ምርታማነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ የካፋ ዞን አስተዳደር ጥሪ አቀረበ

የዞኑ ግብርና፣ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ መምሪያ ግምገማ ነክ የንቅናቄ መድረክ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቦንጋ ከተማ አካሂዷል፡፡ በመክፈቻው ንግግር ያደረጉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በዞኑ ያሉ አቅሞች በመለየት በግብርናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ማነቆዎች በመፍታት ምርትና ምርታማነት ለማረጋገጥ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ልሰሩ እንደሚገባ አሳሰበዋል፡፡ የመምሪያው ሀላፊ አቶ ጋዎ አባመጫ በበኩላቸው በበጋ መስኖ ስንዴ፣ በመደበኛ…

Read More

በክልል ማዕከል አጠቃላይ 59 አመራሮችን ከኃላፊነት የማንሳት፣ የማሸጋሸግ እና በአዲስ መልክ ማደራጀት ሥራ ተሠርቷል፦አቶ ፍቅሬ አማን

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ክልላዊ የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው በብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት በተቀመጡ አቅጣጫዎች መሠረት ከክልል እስከ ታችኛው መዋቅር ያሉት አመራሮች የግምገማና የምዘና መድረክ በጥብቅ ዲስፕሊን በመምራት አመራሩን በተገቢው መመዘን መቻሉን አስታውሰዋል። ግምገማው የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምን መነሻ በማድረግ የ2018 የፓርቲና…

Read More

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዲዮን ሳር በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዲዮን ሳር በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። ጊዲዮን ሳር ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው የኢትዮጵያ እና እስራኤልን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ውይይቶችን ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ…

Read More

ኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ቶን በላይ የቡና ምርት አግኝታለች

ኢትዮጵያ እየተጠናቀቀ ባለው የበጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ቶን በላይ የቡና ምርት ማግኘቷን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል። ባለስልጣኑ ሕገ-ወጥ የቡና ንግድን መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከፌዴራልና ከክልሎች የፀጥታ፣ ከግብርናና ንግድ ዘርፎች ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፤ የቡና ምርትን ከማሳደግ አንፃር በርካታ ስራዎችን እየተሰሩ በመሆኑ ውጤት…

Read More

በክልሉ የተከናወኑ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚብሺን ተከፈተ

በክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተዘጋጀዉ ይህ ኤግዚብሺን በክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ። ፎቶ ኤግዚቢሽኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታና ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በጋራ ከፍተዋል። የፎቶ ኤግዚቢሽኑ በክልሉ በ2016 ግማሽ ዓመት በክልሉ መንግስት ታቅደው የተከናወኑ የልማት ስራዎች…

Read More

በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እየተከናወኑ ያሉ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አፈጉባኤዎች ተናገሩ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው የጋራ ፎረም እየተሳተፉ የሚገኙ የክልሎች እና ከተማ አስተዳደር አፈጉባኤዎች በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እየተከናወኑ ያሉ የግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባእንደሚገባ ተናግረዋል። የፎረሙ ተሳታፊ አፈጉባኤዎች በቦንጋ ዩኒቨርስቲ የሙዝ ልማት፣ የሌማት ትሩፋት አንዱ አካል የሆነውን የከብቶች እርባታ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ስራዎች እና በመማር ማስተማሩ ዘርፍ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች…

Read More

ቻይናን እየጎበኘ ያለው የኢትዮጵያ ልዑክ ከሀገሪቱ ኮሚኒስት ፓርቲ የኦርጋናይዜሽን ዲፓርትመንት ጋር የልምድ ልውውጥ ውይይት አደረገ

በቻይና ጉብኝት እያደረገ የሚገኘውና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ፣ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የፓርቲው ዋና ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ የተመራው ልዑክ ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የኦርጋናይዜሽን ዲፓርትመንት ጋር የልምድ ልውውጥ ውይይት አድርጓል። አቶ አደም ፋራህ በልምድ ልውውጡ፥ ብልጽግና አዲስ ፓርቲ ቢሆንም በመላ ሀገሪቱ መዋቅር ዘርግቶ የተደራጀ ስራ ለመስራትና የአባላቱን አቅም…

Read More

ተስማሚ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ በዕውቀት ላይ የተመሰረቱ የምርምር ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ

ተስማሚ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ በዕውቀት ላይ የተመሰረቱ የምርምር ስራዎችን እየሰራ መሆኑን በኢትዮጵያ የግብርና የምርምር ኢንስቲትዩት የቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታውቀዋል፡፡ በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል በ1965 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ አካባቢ ያለውን የቅመማ ቅመም ምርት እንዲያስተባብር እንደ ሀገር የተቋቋመ የምርምር ተቋም መሆኑን የምርምር ማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ደረጀ ቱሉ ገልፀዋል፡፡ ምርምር ማዕከሉ በተለያዩ…

Read More

“ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ሉዓላዊት ሀገር መሆን ችላለች” – ፕ/ር ፍሬው መክብብ

ኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችላትን ሥራ እያከናወነች ስለመሆኗ ይነሣል። ይህም የገጠሩን የኢኮኖሚ አቅም በፍጥነት እና በፈጠራ በማንቀሳቀስ አርሶ አደሩን ማዕከል ያደረገ ልማትን ለማረጋገጥ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት መጽሐፍ ላይ ጠቅሰውታል። በዚሁ እሳቤ መሠረት ባለፉት ዓመታት በስንዴ ልማት ዘርፍ ላይ የተሰጠው ትኩረት ውጤታማ ሆኗል። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ዓመታዊ…

Read More

በተወሰዱ ርምጃዎች የዋጋ ንረቱ ቀንሷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በተወሰዱ የተለያዩ ርምጃዎች የዋጋ ንረቱ እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው። በማብራሪያቸውም፤ በተወሰዱ ርምጃዎች የዋጋ ንረቱ መቀነሱን ተናግረዋል። ለዚህም በምክንያያትነት የሚጠቀሱት ከአቅርቦት አንጻር በግርብርና ዘርፍ በስፋት መሠራቱ፣ የገበያ ትስስርም ቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን በማስፋት ሻጭና ሸማችን በቀጥታ…

Read More