የግብርና ምርትና ምርታማነትን በመጨመር የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል- ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብር ቢሮ በምግበ ስረዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ትብብር በካፋ ዞን፣ አዲዮ ወረዳ በኖራ የታከመ የመኸር ስንዴ ማሳ የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል። በክልሉ የግብርና ምርትና ምርታማነትን በመጨመር የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ በአርሶአደሩ ማሳና በማሰልጠኛ ተቋማት በምርምር በመታገዝ እና የተሞላ ግብዓትን በመጠቀም የተጀመረው ተግባር አበረታች ውጤት እያሳየ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ነው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር…
የስራ እድል ፈጠራን በተመለከተ
በተያዘው በጀት ዓመት ለ4 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር እቅድ ተይዟል፡፡ከዚህም ውስጥ 700 ሺህ ለሚሆኑት የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ለመፍጠር እቅድ የተያዘ ሲሆን፤ ባለፉት ሶስት ወራት ለሰለጠኑ ለ100 ሺህ ዜጎች በውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ተፈጥሯል፡፡ ኮዲንግ እና የመረጃ ትንተናን ጨምሮ በርቀት ስራዎች ደግሞ ለ26 ሺህ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል፡፡
የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል የኢትዮጵያዊያንን የመከባበር ኃይል ያሳየ መድረክ ነው – የበዓሉ ታዳሚዎች
የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል የኢትዮጵያዊያን የአንድነትና የመከባበር ኃይል የሚያሳይ ትልቅ መሰባሰቢያ መድረክ ነው ሲሉ የበዓሉ ታዳሚዎች ገለጹ። በበዓሉ ላይ ለመታደም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በባህላዊ አልባሳት አጊጠው አዲስ አበባ የተገኙ በርካታ ሰዎች በሆራ ፊንፊኔ በመሰባሰብ የኢሬቻ በዓልን እያከበሩ ነው። ከአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከአገር ውጪ የሚመጡ እንግዶች በጋራ ተሰባስበው የሚገናኙበት ታላቅ ሁነት መሆኑን የሚናገሩት የበዓሉ ታዳሚዎች፤…
በግብርናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለይቶ በመፍታት ምርትና ምርታማነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ የካፋ ዞን አስተዳደር ጥሪ አቀረበ
የዞኑ ግብርና፣ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ መምሪያ ግምገማ ነክ የንቅናቄ መድረክ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቦንጋ ከተማ አካሂዷል፡፡ በመክፈቻው ንግግር ያደረጉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በዞኑ ያሉ አቅሞች በመለየት በግብርናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ማነቆዎች በመፍታት ምርትና ምርታማነት ለማረጋገጥ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ልሰሩ እንደሚገባ አሳሰበዋል፡፡ የመምሪያው ሀላፊ አቶ ጋዎ አባመጫ በበኩላቸው በበጋ መስኖ ስንዴ፣ በመደበኛ…
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ብዝሃ-ዘርፍ እንዲሸጋገር የተነደፈው ፖሊሲ ውጤታማ ሆኗል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ብዝሃ-ዘርፍ እንዲሸጋገር የተነደፈው ፖሊሲ በእጅጉ ውጤታማ ሆኗል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ፤ መንግስት ከሕዝብ ጋር ተሳስሮ ልማት እንዲያመጣ ግልጽ አቅጣጫ የተቀመጠው ከለውጡ ወዲህ መሆኑን ገልጸው÷ ለአብነትም መንግስትና ህዝብ…
በአራት ክልሎች የተካሄደው የ6ኛው ዙር ቀሪና እና የድጋሚ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በተሳካ መልኩ ተጠናቋል፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
በአራት ክልሎች የተካሄደው የ6ኛው ዙር ቀሪና እና የድጋሚ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በተሳካ መልኩ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የ6ኛው ዙር ቀሪና እና የድጋሚ ምርጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በዛሬው ዕለት ተካሂዷል። አጠቃላይ የምርጫውን ሂደት በተመለከተም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ መግለጫ ሰጥተዋል። በ6ኛ ዙር ጠቅላላ ሀገራዊ…
በተወሰዱ ርምጃዎች የዋጋ ንረቱ ቀንሷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
በተወሰዱ የተለያዩ ርምጃዎች የዋጋ ንረቱ እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው። በማብራሪያቸውም፤ በተወሰዱ ርምጃዎች የዋጋ ንረቱ መቀነሱን ተናግረዋል። ለዚህም በምክንያያትነት የሚጠቀሱት ከአቅርቦት አንጻር በግርብርና ዘርፍ በስፋት መሠራቱ፣ የገበያ ትስስርም ቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን በማስፋት ሻጭና ሸማችን በቀጥታ…
በኅብረ ብሄራዊነት የደመቀው የቤንች ብሄር የዘመን መለወጫና የምስጋና (ቢስት ባር) በዓል።
በቢስት ባር በዓል ተጋባዥ እንግዶች እና ጎረቤት ህዝቦች በባህል አልባሳት ደምቀው በመገኘት በዓሉን በጋራ እያከበሩ ይገኛሉ። ተጋባዥ እንግዶቹ ባህላቸውን የሚወክሉ ክኑቶችን በመድረኩ በማሳየት፣ ቢስት ባር የጋራ፣ የአንድነትና የመሰባሰብ በዓል መኾኑን በአደባባይ እያሳዩም ይገኛል። በበዓሉ ላይ፣ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የደቡብ ሱዳን ተማሪዎችና ማኅበረሰብ ተወካዮች እና ሌሎች የውጪ ሀገራት ዜጎችም ታድመዋል። በዕድገቱ በዛብህ
በርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ ዳውሮ ዞን ገባ
በልዑኩ የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ይገኙበታል። የሥራ ኃላፊዎቹ ታርጫ ከተማ ሲደርሱ የከተማው ነዋሪዎች፣ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ልዑካኑ በዳውሮ ዞን በሚኖራቸው ቆይታ በቀጣዮቹ ቀናት የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውሮ እንደሚጎበኙና የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን እንደሚያስመርቁ ይጠበቃል። በዕድገቱ በዛብህ
