Trendings

የኢትዮጵያ ፈተናዎችን ሁሉ የተሻገረ ያለመበገር ፅናት የምጣኔ ሀብት መረጋጋትንና ምርታማነትን ባስቀደሙት በመዋቅራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎቿ ማሳያነት ይገለጣል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)::

የኢትዮጵያ በፈተናዎች ሁሉ የተሻገረ ያለመበገር ፅናት የምጣኔ ሀብት መረጋጋትንና ምርታማነትን ባስቀደሙት በመዋቅራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎቿ ማሳያነት ይገለጣል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ። በብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን በሚመራው ስራ ምክክር እና እርቅ የሰላም ፍላጎታችን እና ተምኔታችን ማጠንጠኛ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል። ትምህርትን ተደራሽ በማድረግ ብሎም ወጣቶችን በማብቃት ኢትዮጵያ ሁለት ሚሊዮን አዳዲስ ስራዎችን ለመፍጠር እንዳለመችም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር…

Read More

የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ ዋና ዋና የትኩረት ነጥቦች ላይ የምክክር መድረክ በሚዛን አማን እየተካሄደ ነው።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታሪኩ አካሉ የለውጡ መንግስት ለንግድና ኢንቨስትመንት ዕድገት የፈጠረውን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የክልሉን ኢንቨስትመንት በመለየት፣ በማጥናት እና ልማታዊ ባለሀብቶችን በመደገፍ በዘርፉ ውጤታማ ተግባራትን ለማከናወን መቻሉን በመክፈቻ ንግግራቸው አንስተዋል። በክልሉ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጮችን በመለየትና በማጥናት በዘርፉ የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ የሀገራችንን ብልፅግና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት ላይ በትኩረት…

Read More

ጉልበት ቆጣቢው የሩዝ ምርት – በሸካ ዞን

መንግሥት የአገር ውስጥ ገበያ ፍላጎትን በሀገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን ትኩረት አድርጎ እየሰራበት ካለው የብርዕ ሰብሎች አንዱ ሩዝ ነው። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልም በዘንድሮው የምርት ወቅት 13 ሺህ 452 ሄክታር መሬት በሩዝ ዘር ተሸፍኗል። በሸካ ዞን ቆይታችንም በአርሶአደሩ ዘንድ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሩዝ እርሻ ተመራጭ እየሆነ መምጣቱን መመልከት ተችሏል። በዞኑ በዘንድሮው መኸር 2 ሺህ የሚጠጋ…

Read More

የሀገራዊ ምክክሩ ኮሚሽን የአጀንዳ ቀረጻና የምክክር አስተባባሪ አቶ ተመስገን አብዲሳ አጀንዳና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል ።

አቶ ተመስገን አብዲሳ ለኮሚሽኑ በአጀንዳነት የሚቀርቡ አጀንዳዎች አጀንዳ የሚያስብላቸው መገለጫ ባህሪያቸው፣ የአጀንዳዎቹ መዳረሻቸው የት እንደሆነ፣ የአጀንዳ ባህሪያትስ ምንድናቸው? የኮሚሽኑ የአጀንዳነት መስፈርት ምን ምንድ ናቸው ? በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለሚዲያ ማብራሪያ ሰጥተዋል ። አቶ ተመስገን በሰጡት ማብራሪያ በሀገር አቀፉ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ በመግቢያው የተገለጸውን ጉዳይ መሠረት በማድረግ ልዩነቶች መኖራቸውንና ለምክክሩ ምክንያት መሆናቸውን አብራርተዋል።…

Read More

የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል የኢትዮጵያዊያንን የመከባበር ኃይል ያሳየ መድረክ ነው – የበዓሉ ታዳሚዎች

የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል የኢትዮጵያዊያን የአንድነትና የመከባበር ኃይል የሚያሳይ ትልቅ መሰባሰቢያ መድረክ ነው ሲሉ የበዓሉ ታዳሚዎች ገለጹ። በበዓሉ ላይ ለመታደም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በባህላዊ አልባሳት አጊጠው አዲስ አበባ የተገኙ በርካታ ሰዎች በሆራ ፊንፊኔ በመሰባሰብ የኢሬቻ በዓልን እያከበሩ ነው። ከአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከአገር ውጪ የሚመጡ እንግዶች በጋራ ተሰባስበው የሚገናኙበት ታላቅ ሁነት መሆኑን የሚናገሩት የበዓሉ ታዳሚዎች፤…

Read More

«የሜኔ ሻዴ ባሮ» የመቻቻል እና የአብሮነት እሴት ማሳያ::

የካፈቾ ብሄር ከጥንት ጀምሮ የራሱ የቀን አቆጣጠር ያለው ሲሆን «የሜኔ ሻዴ ባሮ» በብሄሩ ዘንድ ከአሮጌው ዘመን ወደ አዲሱ መሸጋገርያ ነው። ታላላቅ የብሔሩ ተወላጆችም ከጥንት ጀምሮ በራሱ ስርአትና ወግ ለትውልድ ሲተላለፍ መቆየቱን ያወሳሉ። በዓሉ ዘመን የሚለወጥበት፣ ከአሮጌው ወደ አዲስ የሚታለፍበት፣ ወቅት ስለመቀየሩ ማስታወሻ ይሆን ዘንድ ከመከበሩ ባሻገር አያሌ ትርጉም ያላቸው ተግባራት የሚከናወኑበት ነው። የነፃነት ማሳያ ተደርጎ…

Read More

የክልሉን ሕዝቦች የጤና ደህንነትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት ውጤት ማስመዝገባቸውን ቢሮው አስታወቀ

​በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመሆን በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት የእናቶችና ሕፃናት ጤና አገልግሎት፣ የወባ በሽታ ጫና መቀነስና የጤና መድህን ተደራሽነትን በማረጋገጥ ረገድ ስኬታማ ተግባራት ማከናወኑን አስታወቀ። ​የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም እንደገለጹት፤ በክልሉ የእናቶችንና የሕፃናትን ጤና ለመጠበቅ በተደረገው ጥረት የቅድመ ወሊድ ክትትል አገልግሎት ከፍተኛ ውጤት…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢንዱስትሪ ዘርፍን በተመለከተ የሰጡት ምላሽና ማብራሪያ:-

በኢንዱስትሪው ዘርፍ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ መንግስት ጣልቃ በመግባት የኢኮኖሚ መሻሻያ አድርጓል፤ በዚህም ተጨባጭ ውጤት ተገኝቷል፣ የሀይል አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ በተከናወኑ ተግባራት በዘርፍ ኢነርጂ 100 ፐርሰንት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፣ ከአምናው ጋር ሲነፃፀር በኢንዱስትሪው ዘርፍ 50 በመቶ የሀይል አቅርቦት ጭማሪ ተደርጓል፣ ከግብዓት ጋር እንዲሁም ከኢንዱስትሪ መሬት አቅርቦት ጋር በተያያዘ መንግስት በርካታ ስራዎችን አከናውኗል፣ ኢትዮጵያ…

Read More

በግብርናው ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው ስኬት በማስቀጠል ከተረጂነት መላቀቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው – ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)

በግብርናው ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው ስኬት በማስቀጠል ከተረጂነት መላቀቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች ዘርፈ-ብዙ ጸጋዎች ያሏት ሀገር መሆኗን ተናግረዋል፡፡ እነዚህን ጸጋዎች በሚፈለገው ደረጃ ወደ ልማት መቀየር አለመቻላችን ደግሞ ከተረጅነት እንዳንወጣ አድርጎን ቆይቷል ነው ያሉት፡፡ አሁን ላይም ያሉንን ጸጋዎች በማልማት ከተረጂነት ወደ…

Read More

በክልሉ በመሠረተ ልማት እና በማህበራዊ ዘርፎች የህዝብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ተግባራትን ማከናወን ተችሏል።ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በብልጽግና ፓርቲ የመጀመሪያው ጉባኤው አቅጣጫ መነሻ በክልሉ በመሠረተ ልማትና ማህበራዊ ዘርፎች በተሰሩ ሥራዎችና በተገኙ ውጤቶች ላይ ከሚዲያዎች ጋር ቆይታ አድርጓል። ርዕሰ መስተዳድሩ በቆይታቸውም፤ባለፉት ሶስት ዓመታት በመሠረተ-ልማት እና በማህበራዊ ዘርፎች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ሥራዎች መከናወናቸውና በዚህም እምርታዊ ውጤቶች መመዘገባቸውን ገልጸዋል። በክልሉ ሰፊና ትልቁ ተግዳሮት…

Read More