በከተማው የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሻሻል በተሰጠው ትኩረት አዎንታዊ ለውጥ መመዝገቡ ተገለጸ
በዳውሮ ዞን፣ ታርጫ ከተማ የሚስተዋለውን ስር የሰደደ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሻሻል የባለድርሻ አካላት በሰጡት ትኩረት አውንታዊ ለውጥ መመዝገቡን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ። የታርጫ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዳዊት ወንድሙ፥ የዞኑ ዋና ከተማና የክልሉ ብዝሀ ማዕከል በሆነችሁ የታርጫ ከተማ የሚስተዋለውን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት በዘላቂነት ለማሻሻል የክልሉ መንግሥት ሌሎች የባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ባደረገው ርብርብ አሁን ላይ…
