Trendings

የሸካ ዞን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል ።

ምክርቤቶች የህዝብ ሉአላዊነት መገለጫ እንደመሆናቸው መጠን የህዝብ ልማት ፣ ሰላምና የመልካም አሰተዳደር ችግሮች መፈታታቸው ክትትል ያደርጋሉ ያሉት የሸካ ዞን ምክር ቤት ዋና አፌ -ጉባኤ የተከበሩ አቶ ዮሐንስ ካሳሁን ምክር ቤቱ በ2015 በጀት ዓመት በሰክተሮች ክትትል እና ቁጥጥር ስራን በማጠናከር የተግባር አፈፃፀም ዉጤታማ እንዲሆን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማከናወኑን ገልፀዋል። በበጀት ዓመቱ በዞኑ በርካታ የልማትና መልካም አስተዳደር…

Read More

በዶሮ ፣ በበግ እርባታና በዓሳ ሀብት ልማት መስክ የተሰማሩ ሴቶች፣ ወጣቶችና አርሶ አደሮች ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናገሩ።

ሀገራዊዉ የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ የእያንዳንዱ ቤተሰብ ብልጽግና ማረጋገጫ መሠረት ተደርጎ አርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩን በላቀ ደረጃ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል። ኢኒሼቲቩ የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን በማሳደግ ሀገራዊ ዕድገትን እውን ለማድረግ መሠረት የጣለ ነዉ። በካፋ ዞን በጎባ ወረዳ ያነጋገርናቸው አንዳንድ በማህበር የተደራጁ ሴቶች፣ ወጣቶችና አርሶ አደሮች በዶሮ ፣ በበግ እርባታና በዓሳ ሀብት…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በተገኙበት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ እየተካሄደ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በስብሰባው ላይ የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡም ይጠበቃል፡፡

Read More

በሀገር አቀፍ ደረጃ በተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች ከ300 በላይ ፕሮጀክቶች ተጠናቀዋል – የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ60 በላይ ከተሞች ላይ እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ከ300 በላይ ፕሮጀክቶች በመጀመሪያው ዙር መጠናቀቃቸውን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ። የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ከተሞች ተመራጭ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት መዳረሻ እንዲሆኑ ታቅዶ እየተተገበረ የሚገኝ የልማት ፕሮግራም ነው፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከናወነውን የኮሪደር ልማት ስራዎች አስመልክቶ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ሔለን ደበበ ከኢዜአ ጋር ቆይታ…

Read More

ሀገራዊ ለውጡ ከመንግስት ብቻ የነበረውን የተግባቦት ፍሰት በመቀየር ህዝብን ያሳተፈ የኮሙኒኬሽን ሥርዓት እንዲገነባ አድርጓል፦ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

ከ7 ዓመታት በፊት የተደረገው ሀገራዊ ለውጥ ከመንግስት ብቻ የነበረውን የተግባቦት ፍሰት በመቀየር ህዝብን ያሳተፈ፣ ተገቢ እና ወቅታዊ መረጃ ለማህበረሰቡ የሚሰጥ የኮሙኒኬሽን ሥርዓት እንዲገነባ ማድረጉን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡ ለውጡ ኢትዮጵያ ከነበራት ኋላ ቀር የፖለቲካ ባሕል ተላቃ በሃሳብ የተመሰረተ የፖለቲካ ሥርዓት እንዲኖራት ያስቻለ መሆኑን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ የሚዲያ ብሎም የተቋማትን ነፃነት ማረጋገጥ በለውጡ…

Read More

በቀጣዮቹ 10 ቀናት በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች የተሻለ የዝናብ ስርጭት ይኖራል- ኢንስቲትዩቱ

በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች የተሻለ የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። በዚሁ መሰረት በሚቀጥሉት አሥር ቀናት ምሥራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ጅማ፣ ኢሉአባቦር፣ ማዕከላዊ እና ምዕራብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ አሶሳ፣ ካማሺ፣ መተከል እና የማኦ ኮሞ ልዩ ዞን የተሻለ የዝናብ መጠን እንደሚኖራቸው የኢንስቲትዩቱ መረጃ አመላክቷል፡፡…

Read More

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አለልኝ አዘነ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ::

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። የባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ እንዳስታወቀው፤ አለልኝ በጉዳት ምክንያት ከቡድኑ ተለይቶ በትውልድ ስፍራው አርባ ምንጭ ለእረፍት የሄደ ሲሆን ትናንት ምሽት በድንገት ህይወቱ አልፏል። አለልኝ የእግርኳስ ህይወቱን በአርባምንጭ ከተማ ክለብ የጀመረ ሲሆን በባህርዳር ከተማ ለሁለት ዓመታት ምርጥ ጊዜ…

Read More

ክልሉ ከተመሠረተ ወዲህ ለከተሞች የተለያዩ ደረጃ እና ዓይነት ያላቸው 86  ፕላኖች ተዘጋጅተዋል-የክልሉ ከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት

የከተማ ትልቁ ሀብት መሬት ነው።የከተሞች ውስን ሀብት የሆነው የከተማ መሬትን በአግባቡ ማስተዳደር ከተማን የሚመጥን ፕላን ማዘጋጀት ያስፈልጋል። የከተማ ፕላን የአንድን ከተማ እና የአካባቢውን የወደፊት ዕድገት የህዝቡን ጥቅም እና የከተሞችን እድገት መሰረት በማድረግ እንዲመራ ተደረጎ የሚዘጋጅ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ሲሆን በይዘት ደረጃ የከተማውን መሬት አጠቃቀም፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ታሪካዊ፣ የፊዚካላዊና ሌሎች ጉዳዮችን ያካትታል፡፡ ከተሞች በፕላን ሲመሩ ለከተማው…

Read More

ምግብና ሥርዓተ ምግብን ለማረጋገጥ የብዝሀ ሴክተሮች ቅንጅታዊ አሠራር መጠናከር እንዳለበት ተገለጸ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የምግብ ሥርዓት ሽግግር ፍኖተ ካርታ ማስጀመሪያ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ አቶ ሰብስቤ ሻዎኖ ባደረጉት ንግግር፣ በክልሉ ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ የምግብና ሥርዓተ ምግብ ካውንስል ተቋቁሞ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ሰብስቤ ሻዎኖ እንደገለጹት፣ የምግብና ሥርዓተ ምግብ ጉዳይ የአንድ ሴክተር ብቻ ሳይሆን የብዝሀ…

Read More