የክልሉ መንግስት በትምህርት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሰራ ነው -ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት “ትውልድ በመምህራን ይቀረጻል፣ ሀገር በትምህርት ይበለጽጋል” በሚል መሪ ቃል ክልላዊ ማጠቃለያ የመምህራን ውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በመድረኩ እንደገለጹት በክልሉ የትምህርት ስብራት መጠገን፣ የትምህርት ጥራት ማሻሻል እና መምህራን የሚያነሷቸው ጥያቄዎችን መፍታት የክልሉ መንግስት ትኩረት ሰጥተው የሚሰራባቸው ጉዳዮች መሆናቸዉን ገልጸዋል። በክልሉ ባለፉት ጊዜያት…
