የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተግባራትና ኃላፊነቶች
ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ህገ መንግሥት አንቀጽ 102 መሠረት የተቋቋመ ገለልተኛ ህገ መንግሥታዊ ተቋም ነው። ቦርዱ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ የፌዴራል እና የክልል ጽህፈት ቤቶችን ያደራጀ ሲሆን በሁሉም ክልልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች እንዲሁም በፌደራል ደረጃ ቢሮዎች አሉት። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስድስት ሀገራዊ ምርጫ ያስፈጸመ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ አራት የአካባቢ ምርጫ፣ እና ስምንት ሕዝበ ውሳኔዎችን…
