የኢትዮጵያ አየር መንገድና የቦይንግ ትብብር የኢትዮጵያና የአሜሪካንን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ያጠናክራል – አምባሳደር ኧርቪን ሆሴ ማሲንጋ::
የኢትዮጵያ አየር መንገድና ቦይንግ የደረሱበት የትብብር ደረጃ የኢትዮጵያና የአሜሪካንን ምጣኔ ኃብታዊ ግንኙነት ለማጠናከር ትልት አስተዋጽኦ ያደርጋል ሲሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ሆሴ ማሲንጋ ገለጹ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአፍሪካ በዓይነታቸው የመጀመሪያ የሆኑ 20 ቦይንግ 777 ኤክስ 9 የተሰኙ ግዙፍ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግ ኩባንያ ጋር በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ የመግባቢያ ሥምምነት አድርጓል። በመርኃ-ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ…
