Trendings

Getenesh Gebeyehu

ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ መካሔድ ጀመረ

ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ የመክፈቻ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ መካሔድ ጀምሯል። በጉባኤው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ የጣሊያን ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ፣ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር መሃመድ አሊ የሱፍ ተገኝተዋል። በተመሳሳይ የኬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ፣ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ፣ የኮሞሮስ ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒ፣ የላይቤሪያ…

Read More

በአንድ ጀንበር ተከላ ከ21 ሚሊዮን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በ2017 ዓ/ም የአንድ ጀንበር ተከላ ክልላዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ከ21 ሚሊዮን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው እንደተናገሩት የ2017 ክልላዊ የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ በዕለቱ ዘርፈብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ከ21 ሚሊዮን በላይ ችግኞች…

Read More

ቆይታ ከእኛ ጋር

መንግስት ሀገራዊ  የልማት ግቦችን ለማሳካት እና የህዝቦችን ሁለንተናዊ ፍላጎቶች ለመድረስ ከተለያዩ ምንጮች የተገኘውን ሀብት በኃላፊነትና ተጠያቂት ስሜት ለህዝቡ ማድረስ የሚችል የፋይንስ አሠራር ስርዓትን ለመዘርጋት ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንዳለ ይገለጻል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተመሠረተ ወዲህ ሀገራዊ የአሰራር ማሻሻያዎችን መሠረት ያደረጉ የተለያዩ አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን በማውጣት ከዚህ ቀደም ይታዩ የነበሩ ክፍተቶችን ለማረም የተከደበት እርምጃ የሚደነቅ…

Read More

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያንን ያስተሳሰረ ትውልድ ተሻጋሪ ብርሃን ነው ሲሉ የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪ ገለጹ

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በህብረት የተሳካ የኢትዮጵያ የማንሰራራት መገለጫ የይቻላል ማሳያም ጭምር ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ በብዙ ልፋትና መስዋዕትነት የተገነባው ታላቁ የኢትዮጰያ ህዳሴ ግድብ በመስከረም ወር እንደሚመረቅ ማብሰራቸው ይታወሳል፡፡ ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ የጋራ ተጠቃሚነት አቋሟ የጸና መሆኑን መናገራቸውም እንዲሁ። ኢዜአ በታላቁ…

Read More

51 ማሊዮን ችግኞችን በሴቶችና ህፃናት በማስተከል የአየር ንብረት ለውጥ እንድስተካከል የበኩላችንን ሚና እንወጣለን፦ወ/ሮ ገነት መኩሪያ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ “በመትከል እናሰራራለን ” በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ ያለው የዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካል የሆነውና ሴቶችና ህጻናት ብቻ የሚሳተፉበት “ኢትዮጵያ በሴቶችና ህፃናት አረንጓዴ ትለብሳለች” በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ መርሀ -ግብር በቦንጋ መምህራን ኮሌጅ አከናውኗል። በመርሀ-ግብሩ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ…

Read More

በአንድ ጀምበር ሚሊዮኖችን በመትከል የማንሰራራት ታሪካዊ ጉዞ አካል እንሁን፦ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ኢትዮጵያን ወደ ነበራት ጥንታዊ የደን ሽፋን በመመለስ አረንጓዴ ካባ ለማልበስ የጀመርነው ጥረት 7ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል፤ 7ኛ ዓመት የጥረታችንን ጅማሮ የምንዘክረዉ ደግሞ በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ነው፡፡ ባለፉት 6 ዓመታት የአረንጓዴ ዐሻራ ጉዟችን ኢትዮጵያውያን ከሁሉም አቅጣጫ፣ ከደጋ እስከ ቆላ በጋራ ባደረግነዉ ጥረት 40 ቢሊዮን ችግኞች በላይ ተክለናል፤ የኢትዮጵያን የደን ሽፋንም እስከ ባለፈዉ ዓመት…

Read More

በግብርናው ዘርፍ የሚደረጉ ምርምሮች ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር እያስቻሉ ነው ተባለ

በግብርናው ዘርፍ የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች የዘርፉ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር እያስቻሉ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ገለጸ። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ በግብርናው እሴት ሰንሰለት ላይ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን በጥናትና ምርምር መለየት፣ ለማነቆዎቹ የመፍትሔ ሃሳብ ማመንጨት ላይ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ በዘርፉ የመፍትሔ ሃሳብ ማመንጨት ብቻ ሳይሆን የመፍትሔ ሃሳቦች ገቢራዊ እንዲሆኑ በማስቻል ምርትና ምርታማነት እንዲያድግ እየሰራ…

Read More

ኢቢሲ በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ የራሱን አሻራ ያኖረ ትልቅ ተቋም ነው፡ – ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)

ኢቢሲ ኢትዮጵያን በመገንባት እና አንድነቷን በማጠናከር በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ የራሱን አሻራ ያኖረ ትልቅ ተቋም ነው ሲሉ በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድ ካቲንግ ኮርፖሬሽን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ታርጫ ከተማ ተጨማሪ የይዘት ምንጭ የሆነውን አዲስ ስቱዲዮ በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡ በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ…

Read More

ኢቢሲ በህዝብ ወገንተኝነትና በሀገር ፍቅር በማገልገል የሚታወቅ ግዙፍ ተቋም ነው፦ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

የኢቢሲ ወደ ይዘት ጉዞ አካል የሆነው አዲሱ የታርጫ የኢቢሲ ስቱዲዮን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) እና የኢቢስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ታደሰ በተገኙበት ተመርቆ ስራ ጀምረዋል ። በምረቃ ስነስርዓት ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ክልሉ…

Read More

የኢቢሲ ታርጫ ስቱዲዮ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የክልሉ ብዝሃ ማዕከል አንዱ በሆነው በታርጫ ከተማ የተገነባው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (የኢቢሲ) ስቱዲዮ በይፋ ተመርቆ ስራ ጀምረዋል። የኢቢስ ወደ ይዘት የጉዞ አካል የሆነው አዲሱ የኢቢሲ ታርጫ ስቱዲዮን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) እና የኢቢስ ዋና…

Read More