መጋቢት 24 በሀገራችን ታርክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሠላማዊ የስልጣን ሽግግር የተደረገበት ከመሆኑም በላይ ክልሉ አንዱ የለውጡ ፍሬ ማሳያ ነው ፦ አስተያየት ሰጪ አመራሮች
ሀገራዊ ለውጡ የተበሰረበትና 8ኛ ዓመት፤ የለውጡ ፍሬዎችን የሚያንፀባረቁ፤ የሚዘክርና የአገራዊ አንድነትን ጥንካሬ የሚያሳይ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብዝሀ ከተሞች አንዱ በሆነው በቦንጋ በተለያዩ ደማቅ ዝግጅቶች ተካሂዷል። ያነጋገርናቸው የድጋፍ ሰልፉ ታዳሚ አመራሮች መጋቢት 24 ባመጣቸውና በለውጡ መንግስት በተመዘገቡ ድሎች ዙሪያ አስተያየታቸውን ስጥተዋል ። የክልሉ የመንግስት ረዳት ተጠሪ የሆኑት አቶ በላይ ተሰማ መጋቢት…
