የመጋቢት 24 ትሩፋቶች በሚል መሪ ሀሳብ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
መጋቢት 24 በትውልድ ቅብብሎሽ የሚገነባውን ብልፅግና ያፀናል፣ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር፣የመጋቢት 24 አንፀባራቂ ድል ለኢትዮጵያ ብልፅግናና ልዕልና መሠረት ነው እንዲሁም መጋቢት 24 የኢትዮጵያ ከተሞች ትንሳኤ ነው የሚሉ መፈክሮች በሰልፉ ተመልክተዋል። በሰልፉ የታርጫ ማዕከል ክልል ክላስተርና የዳውሮ ዞን አመራሮች እንዲሁም የዞኑ ህዝቦች በመሳተፍ ላይ ናቸው
ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት በማስመልከት በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት አስመልክቶ ከሸካ ዞን ከተወጣጡ የተለያዩ ህብረተሰቦች ጋር በቴፒ ከተማ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል። የድጋፍ ሰልፉ ታዳሚዎች በለውጡ አመታት የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚያመለክቱ መፈክሮችን እያሰሙ ይገኛሉ። ከመፈክሮቹ መካከል ”መጋቢት 24 የኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ የታወጀበት ታሪካዊ ቀን ነው”፣ ”መጋቢት 24 የለውጥ እና የብልጽግና መሠረት ነው” ፣ሀገራዊ ምርጫ የድሞክራሲያዊ ማማና የሉዓላዊነት መገለጫ…
ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በሰልፉ ስፍራ ተገኙ።
በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የክልል፣ የዞን እና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በክብር እንግድነት ተገኝተዋል። ከአራቱም አቅጣጫዎች ከሚመጣው ነዋሪ ጋር በመቀላቀል ወደ መድረኩ የገቡት አመራሮቹ ህዝቡ ለለውጡ ያለውን ደጀንነትና አጋርነት በቅርበት እየተከታተሉ ይገኛሉ። የአመራሮቹ በቦታው መገኘት ለሰልፉ ታዳሚዎች ተጨማሪ መነሳሳትን የፈጠረ ሲሆን፣ በዕለቱ ለውጡንና ቀጣይ የልማት አቅጣጫዎችን በተመለከተ ከአመራሮቹ የሚተላለፉ…
ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት የሚዘክር ደማቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በተገኙበት በቦንጋ ከተማ ደማቅ የድጋፍ ስልፍ እየተካሄደ ይገኛል። በሀገራዊ ለውጡ ለተገኘው አንጸባራቂ ድል እውቅና በሚሰጠው በዚህ የድጋፍ ሰልፍ የመጋቢት 24 ትሩፋቶችን የሚዘክሩ የተለያዩ መልዕክት በሰልፈኞች እየተላለፉ ይገኛል። በህዝባዊ ትዕይንቱ የቦንጋ ከተማ እና ከዞኑ ሁሉም…
በቦንጋ ከተማ ደማቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሠልፍ እየተካሄደ ይገኛል!
የለውጡ ትሩፋቶችን የሚዘክር ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በቦንጋ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የድጋፍ ሰልፍ በለውጡ መንግሥት የተገኙ የመጋቢት 24 ድሎችንና ሁለንተናዊ ለውጦችን የሚዘክር እንዲሁም ለተገኘው ለውጦች እውቅናን የሚሰጥ ነው። የድጋፍ ሰልፋ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የብልጽግና ፓርቲ መሪነት የተመዘገቡ ለውጦችን የሚገልጹ የተለያዩ መልዕክቶች በሰልፈኞቹ እየተላለፈ ነው። ነዋሪዎቹ በለውጡ መንግሥት እየተከናወኑ ላሉ የልማት…
በካርዳችን ዴሞክራሲያዊ መብታችንን እውን ለማድረግ ዝግጁ ነን፡- የካፋ ዞን አርሶ አደሮች
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመምረጥ የሚያስችላቸውን የመራጭነት ካርድ በመውሰድ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን የካፋ ዞን አርሶ አደሮች ገልፀዋል። በዞኑ ጊምቦ ወረዳ የሾምባ ሼካ ቀበሌ አርሶ አደሮች እንደገለጹት የሚመራቸውን ዕጩ ለመምረጥ የሚያስላቸውን የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን ለኢቢሲ ተናግረዋል። ያለፉት 6 ተከታታይ የምርጫ ሂደቶች ተሳትፈው የሚበጃቸውን የፖለቲካ ፓርቲ መርጠናል ያሉት አርሶ አደሮቹ የዘንድሮው ምርጫ ካለፉት ጊዜያት መሻሻሎች የታዩበት ነው…
ከምርጫ ስራዎች ጎን ለጎን ወቅታዊ የኢኒሼቲቭ ተግባራትን በማስተሳሰር አመራሩ በቁርጠኝነት ውጤታማ ስራ መስራት አለበት ፦ አቶ ማስረሻ በላቸው
የደቡብ ምዕራብ ክልል ምክትል ር/መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የካፋ ዞን ጊምቦ፣አዲዮና ቦንጋ ከተማ መዋቅሮች ወቅታዊ የኢኒሼቲቭ ተግባራትና የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት አፈጻጸም ገምግሟል ። ከምርጫ ስራዎች ጎን ለጎን ወቅታዊ የኢኒሼቲቭ ተግባራትን በማስተሳሰር አመራሩ በቁርጠኝነት ውጤታማ ስራ መስራት እንዳለበት የተናገሩት አቶ ማስረሻ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅና የመንግስት ልማት…
የፓርቲውን መንትያ ግቦችን ለማሳካት አባሉ የመሪነት ሚናውን በቁርጠኝነት ሊወጣ ይገባል ፦ አቶ ሳምሶን መለሰ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የቦንጋ ብዝኃ ማዕከል የአስተዳደር ዘርፍ ብልፅግና ህብረት 2018 ዓም 3ኛ ዙር መደበኛ የአባላት ኮንፈረንስ ተካሂዷል። በኮንፈረንሱ የህብረቱ ሰብሳቢ አቶ ሳምሶን መለሰ እንደገለጹት ባለፉት ወራት በፓርቲው የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት በተደረገው ጥረት ተጨባጭና ተስፋ ሰጭ ውጤቶች መመዝገቡ ተገልጿል። በፓርቲው እሳቤዎች በኢኮኖሚ፣በማህበራዊና በፖለቲካ መስኮች አበረታች ውጤቶ መመዝገቡን አንስተዋል። የፓርቲው ተቋማዊ…
የኮሪደር ልማት መሰራት የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን ምቹ ማድረጉን በኮንታ ዞን የጪዳ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
ወ/ሮ አባይነሽ ጥላሁን እና ወጣት የአብስራ አይመሎ የከተማዋ ነዋሪዎች ሲሆኑ የኮሪደር ልማት እሳቤ ሲመጣ ቤቶቻቸውን የሚጎዳና ችግር የሚያስከትል ሆኖ እንደተሰማቸው አውስተው አሁን ላይ በተሰራው ስራ ‘እንኳንም መጣልን’ አልን ማለታቸው ገልፀዋል። የኮሪደር ልማት ስራው ህፃናት፣ ሽማግሌዎችና አቅመ ደካሞች እንደልብ የሚመላለሱበት እየሆነ ይገኛል ያሉት ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውንም ምቹ ማድረጉን አስረድተዋል። ቀደም ሲል መኪና፣ ሞተርና እግረኛ ሁሉም…
