በክልሉ ከተጀመሩ ኢኒሼቲቮች አንዱ የሆነው የሻይ ተክል ልማት ስራን ዉጤታማ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ ፡፡
በዘንድሮው የሻይ ተክል ልማት በአዲስ ማሳ 50ሄ/ር ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ መሆኑም ታውቋል ፡፡ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቡና ሻይና ቅመማቅመም ባለስልጣን ባለፉት 11 ወራት በሻይ ተክል ልማት ስራዎች የሚበረታቱ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጿል ፡፡ የባለስልጣን መ/ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በላይ ኮጁዋብ እንደገለጹት የሻይ ተክል ልማት ኢኒሼቲቭ በክልሉ ከተጀመረወዲህ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን…
