የክልሉ የድጋፍና ክትትል ቡድን በካፋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎችና በአንድ ከተማ አስተዳደር ድጋፋዊ ክትትል ያደረገው ቡድን ግብረ-መልስ አቅርቧል::
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር የማታለም ቸኮል የድጋፍና ክትትል ግብር- መልስ ሪፖርት አቅርበዋል ፡፡ የደጋፍና ክትትል ዓላማው በሁሉም መስኮች የተመዘገቡ አበረታች ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠልና ጉድለቶችን ፈጥኖ ማረም የሚያስችል አቅጣጫ ማስቀመጥ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡ በፖለቲካው፣በኢኮኖሚ፣በማህበራዊ እና በአስተዳደር ዘርፎች በተከናወኑት ሥራዎች የተመዘገቡ አበረታችና ተስፋ ሰጪ ውጤቶችንና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ዘርዝረዋል ፡፡…
