በክልሉ የአጀንዳ ማሰባሰብ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ይጀመራል
የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ባዘጋጀው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮችና ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት የአጀንዳ ማሰባሰብ የውይይት መድረክ ከክልሉ ሁሉም ዞኖች የተውጣጡ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎች በካፋ ባህል አዳራሽ ተገኝተዋል። በምክክር መድረኩ ሀገር አቀፍ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘገየ አስፋውና ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ ተገኝተዋል። በታጠቅ አበበ
በግብርናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለይቶ በመፍታት ምርትና ምርታማነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ የካፋ ዞን አስተዳደር ጥሪ አቀረበ
የዞኑ ግብርና፣ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ መምሪያ ግምገማ ነክ የንቅናቄ መድረክ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቦንጋ ከተማ አካሂዷል፡፡ በመክፈቻው ንግግር ያደረጉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በዞኑ ያሉ አቅሞች በመለየት በግብርናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ማነቆዎች በመፍታት ምርትና ምርታማነት ለማረጋገጥ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ልሰሩ እንደሚገባ አሳሰበዋል፡፡ የመምሪያው ሀላፊ አቶ ጋዎ አባመጫ በበኩላቸው በበጋ መስኖ ስንዴ፣ በመደበኛ…
የኢፌዲሪ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በቴፒ ከተማ ቅርንጫፍ በመክፈት በቅርቡ የቡና ላቦራቶሪ እና ሰርቴፊኬሽን አገልግሎት ልጀምር መሆኑ ተገለፀ
ለቅርንጫፉ መከፈት ከፍተኛውን ድርሻ ለተወጡ አካላት በሙሉ ሸካ ዞን አስተዳደር ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል። ከኢፌዲሪ ቡናና ሻይ ባለስልጣን እና ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቡናና ሻይ ባለስልጣን የተውጣጣ የአመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ቡድን በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ተገኝተው የቡና ቅምሻ ላቦራቶሪና ሠርተፊኬሽን ማዕከልን በቴፒ ከተማ ለመክፈት እየተደረገ ያለውን ዝግጅት ምልከታ አድርገዋል። የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ…
በመረጃ የበላይነት የያዘ ሃይልና ሀገር በሌሎች ሁኔታዎች ላይ የማሸነፍ እድሉ ሰፊ ነው – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ
በመረጃ የበላይነት የያዘ ሃይልና ሀገር በሌሎች ሁኔታዎች ላይ የበላይነት የመያዝና የማሸነፍ እድሉ ሰፊ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡ የብሔራዊ ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ በማስተርስ መርሐ ግብር ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል፡፡ በምረቃ መርሐ ግብሩ ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። ም/ጠ/ሚ ተመስገን በምረቃ…
በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የብልጽግና ፓርቲ የልዑካን ቡድን በቻይና የተለያዩ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም የሚያስችል ጉብኝት አደረገ
በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ የሚመራው የፓርቲው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በቻይና የተለያዩ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም የሚያስችል ጉብኝት አደረገ። ቡድኑ በግብርና ምርት ከፍተኛ ውጤት እያገኘች ባለችው ኽናን ግዛት በመገኘት በግብርና ምርታማነት፣ በኢንዱስትሪ፣ በሲቪል አቪዬሽን፣ በገጠር መንደሮች ልማትና በቅርስ፣ ባህልና ታሪክ ጥበቃ እየተከናወኑ ያሉ ውጤታማ ተግባራትን ጎብኝቷል። ቡድኑ በጉብኝቱ በግብርና መስክ በተደረጉ…
ጉልበት ቆጣቢው የሩዝ ምርት – በሸካ ዞን
መንግሥት የአገር ውስጥ ገበያ ፍላጎትን በሀገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን ትኩረት አድርጎ እየሰራበት ካለው የብርዕ ሰብሎች አንዱ ሩዝ ነው። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልም በዘንድሮው የምርት ወቅት 13 ሺህ 452 ሄክታር መሬት በሩዝ ዘር ተሸፍኗል። በሸካ ዞን ቆይታችንም በአርሶአደሩ ዘንድ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሩዝ እርሻ ተመራጭ እየሆነ መምጣቱን መመልከት ተችሏል። በዞኑ በዘንድሮው መኸር 2 ሺህ የሚጠጋ…
የሸካ ዞንን ሰላም በማጽናት በሁሉም ዘርፎች ዉጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ ተገለጸ
የሸካ ዞንን ሰላም በማጽናት በሁሉም ዘርፎች ፊት እንዲወጣና በቀጣይ 5 ዓመታት የተያዙ የልማት ዕቅዶች ዙሪያ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቴፒ ከተማ ውይይት ተካሂዷል የከተማ ኮሪደር ልማቶች፣የመልሶ ማልማት ፣ከተማን ለኢንቨስትመንት ማዘጋጀትና መከታተል በማህበራዊና በኢኮኖሚ ዘርፍ በተለይ አዳሪ ትምህርት ቤት በመክፈት ተወዳዳሪ ትዉልድ ለመፍጠርና በሌሎችም የልማት ሥራዎች ዙሪያ ምክክር ተካሂዷል። በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮዽያ ህዝቦች ክልል በምክትል…
በታሪክ ተመራማሪው አቶ አሰፋ ገብረማርያም እና በአቶ አዕምሮ ገሰሰ የተጻፈ መጸሐፍ በቦንጋ ከተማ ተመረቀ፡
መጸሐፉ የካፈቾ ህዝብ ባህል እና ታሪክ ላይ ያተኮረ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ የመጸሐፉ ደራሲ አቶ አሰፋ ገብረማርያም መጽሐፉ ሰባት ምዕራፎችና 3 መቶ 36 ገጾች ያሉት እንዲሁም የካፈቾ ባህል እና ታሪክ ላይ ያተኮረ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የካፈቾ ብሔር ማንነትን፣ የጎንጋ ህዝቦች ትስስርን፣ ጥንታዊ የካፋ መንግስት አመሰራርንና ሌሎችንም ሀሳቦች ስለማካተቱ ገልጸዋል፡፡ መጽሐፉ ለታዳጊ ደራሲዎች መነሻ እንደሚሆን ገልጸው ፤ ለህትመት እንዲበቃ…
