Trendings

Getenesh Gebeyehu

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሚያከናውነው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ነገ ይጀመራል

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከነገ ጀምሮ የሚካሄደውን የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ በተመለከተ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው እና ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ በጋራ በቦንጋ ከተማ ተገኝተው ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ኮሚሽነሮቹ በመግለጫቸው በምክክር ሂደቱ ቁልፍ ከሆኑ ተግባራት መካከል አጀንዳዎች አካታችና አሳታፊ በሆነ ሂደት የማሰባሰብ እንዲሁም በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ ተወካዮች የማስመረጥ ተግባር በመሆኑ ለዚህም ኮሚሽኑ…

Read More

የክልሉን ሠላም በዘላቂነት ለማጽናት የሚያበረታቱ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተናገሩ።

ይህ የተገለጸው የመልካም አስተዳደርና ህግ ጉዳዮች ዘርፍ ተቋማት የአፈጻጸም ሪፖርት በቀረበበት ነው። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት የአንደኛው ሩብ ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል። የአፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረቡት የርዕሰ መስተዳድሩ የመልካም አስተዳደርና ህግ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑ አቶ አክሊሉ ከበደ የሚያስተባብሯቸውን ተቋማት የአፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል ። ባቀረቡት የአፈጻጸም ሪፖርት በየተቋማቱ የሚያበረታቱ…

Read More

ብኢትዮጵያ በሩሲያ ካዛን እየተካሄደ በሚገኘው የብሪክስ የወጣቶች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ነች።

በስብሰባው ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት የተውጣጣ የልዑክ ቡድን እየተሳተፈ ይገኛል። በወጣቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ዙሪያ የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ ላይ ኢትዮጵያን በመወከል መልዕክት ተላልፏል። የልዑካን ቡድኑ ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ የመተባበር እና የአንድነት መንፈስ እንዲጎለብት ሚናዋን በተገቢው መልኩ እንደምትወጣ ገልጿል። ልዑኩ ከስብሰባው ጎን ለጎን የካዛን ከተማ የወጣት ማዕከላት እና…

Read More

በማጂ ቱም ከተማ አ/ር የማጂ ከተማ የሶላር መብራት አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ ነው ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በማጂ ቱም ከተማ ለዘመናት የህዝብ ጥያቄ የሆነው ይኸው የኤሌክትሪክ አቅርቦት ጥያቄን ምላሽ ለመስጠት መንግስት ትኩረት በመስጠት እየሰራ ይገኛል ። ችግሮቹን ለመቅረፍ የሶላር ቁሳቁስ የያዙ አምስት የጭነት መኪናዎች ከአዲስ አበባ ተነስተው ማጂ ከተማ መድረሳቸውን የማጂ ቱም ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።

Read More

ከደረጃ በታች የሚያመርቱ 14 ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

ከጥራት ደረጃ በታች ምርት በሚያመርቱ 14 ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ ያላቸውን ምርቶች የሚያመርቱ 100 ፋብሪካዎች ላይ የኢንስፔክሽን ስራ ተሰርቷል። በዚህም የ14 ፋብሪካ ምርቶች ከጥራት ደረጃ በታች ሆኖ በመገኘታቸው ርምጃ እንደተወሰደባቸው ተገልጿል። እርምጃ የተወሰደባቸው ፋብሪካዎች የቆርቆሮ፣ የዕቃና የልብስ ሳሙናዎች፣ የአርማታ ብረት፣ ዱቄት…

Read More

#ኢትዮጵያ_እየመከረች_ነው!

#ደቡብ_ምዕራብ_ኢትዮጵያ እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚታየውን አመግባባት ለመፍታት አካታች እና አሳታፊ በሆነ መልኩ ምክክር ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያም ይህንኑ አምናበት ሁሉም ዜጎች የሚሳተፉበት ምክክር በማድረግ ላይ ትገኛለች። እርስዎም ሀሳብዎ ለሀገራችን ችግሮች መፍትሄ እንደሚሆን አውቀው በምክክሩ በንቃት ይሳተፉ! ኮሚሽኑ በመጪው እሁድ ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚጀምረው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ የቅስቀሳና…

Read More

ትምህርት ቤቶች የውስጥ ገቢን ማሳደግ ለትምህርት ጥራት ያለው አስተዋጽኦ የላቀ ነዉ። አቶ አልማው ዘውዴ

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ትምህርት ቤቶች የውስጥ ገቢን ማሳደግ ለትምህርት ጥራት ያለው አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን ገልጸዋል ። በ2016 ዓ/ም በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር በጨታ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በበልግ እርሻ 141 ነጥብ 5 ኩንታል የበቆሎ ሰብል ምርት መገኘት መቻሉን…

Read More

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ ተቋማት ሚናቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው ተመላከተ

ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ በንቃት ለመሳተፍ እና በመድረኩ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ ተቋማት የሚኖራቸውን ሚና ማጠናከር እንዳለባቸው ተገለጸ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የብሪክስ የከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የቴክኒክ ኮሚቴ 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዩ የፖሊሲ አማካሪ አምባሳደር ምኒልክ ዓለሙ እንደተናገሩት፤ ጉባዔው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች አስጠብቋል። ጉባዔው የኢትዮጵያን ጥቅምና ፍላጎቶች ያስጠበቀ፣ አባል ሀገራቱ ለዓለም አቀፍ የፋይናንስ፣ የኢኮኖሚ እና…

Read More

በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ በጣለዉ ከባድ ዝናብ በተከሰተ የመሬት ናዳ አራት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸዉ ማለፋን ፖሊስ አስታወቀ

በዞኑ አዲዮ ወረዳግራዋ ሽሽማ ቀበሌ በሌ ልማት ቡድን ተብሎ በሚጠራበት ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት በጣለዉ ከባድ ዝናብ ባስከተለዉ የመሬት መንሸራተት አራት የአንድ ቤተሰብ አባላት በመኖሪያ ቤት ዉስጥ እንዳሉ ህይወታቸዉ ማለፋን ፖሊስ ገልጿል። በአደጋዉ ሁለት መኖሪያ ቤቶች በናዳዉ መወሰዱን ያመለከተዉ ፖሊስ በአከባቢዉ የሚጥለዉ ከባድ ዝናብ የነፍስ አድኑን ስራ አስቸጋሪ አድርጎታል።

Read More

የዞኑን ልማት በማፋጠን የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሁሉም ተሳትፎና ርብርብ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

ይህ የተባለው በሸካ ዞን ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በትኩረት በሚፈፀሙ ተግባራት ላይ ያተኮረ ውይይት በቴፒ ከተማ እየተካሄደ በሚገኝበት ወቅት ነው። የውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ በወቅቱ እንደተናገሩት የዞኑን ልማትና እድገት ለማፋጠን እንዲሁም የዞኑን ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ርብርብ ወሳኝ ነው ብለዋል። አቶ…

Read More