በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር ይሸፈናል
በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር እንደሚሸፈን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ። ሚኒስትሩ ወቅታዊ የግብርና መረጃዎችን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም፤ በመኸር እርሻው 20 ነጥብ 4 ሚሊየን ሄክታር መሬት በአነስተኛ ይዞታ ባላቸው አርሶ አደሮች መልማቱን አስታውሰው፤ በሰፋፊ እርሻም ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን…
