አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ሀገር የመገንባት ራዕይን ከግብ ለማድረስ ሁለንተናዊ የልማት ዕቅዶቻችን ሳይቆራረጡ ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ፡፡
የፌደራል ተቋማት የሱፐርቪዥን ማጠቃለያ ሪፖርት ግምገማ ዛሬ ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ ከመስክ ምልከታ የተገኙ ሪፖርቶችን ጨምሮ የተቋማት አፈፃፀም ጠለቅ ባለ እና በተደራጀ መልኩ ሪፖርት ቀርቧል፡፡ ዕቅዶች መሬት ላይ ወርደው ሲተገበሩ ምን ውጤት አመጡ፣ በትግበራ ሂደቱ ያጋጠሙ ችግሮች ምን ይመስላሉ፣ እንዲሁም በቀጣይ በመረጃ እና በትንተና የተደገፈ አካሄድ እንዴት መፍጠር እንደሚቻል በመድረኩ ተነስቷል፡፡ በሱፐርቪዥኑ ሪፖርት በመልካም ጅማሮ የታየው ዋንኛው…
