በክልሉ በተደረገው የፀጥታ ሥራ አብዛኛዎቹን የፀጥታ ችግሮች መፍታት ችለናል፦ አቶ ፋጂዮ ሳፒ::
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከጎባ ክላስተር ኩታ ገጠም (ዞኖችና ወረዳዎች) ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ አካሂዷል፡፡ በመድረኩ ላይ በአርብቶ አደር አካባቢዎች (በጎባ ክላስተር) ኩታ ገጠም ዞኖችና ወረዳዎች የሚስተዋለውን የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ የታቀደ ዕቅድ በክልሉ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊና የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ በአቶ ሀብታሙ አለሙ ቀርቦ ውይይት…
