Trendings

Getenesh Gebeyehu

የክልሉ ከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት የከተሞችን መዋቅራዊ ዕድገት የሚመሩ ስትራቴጂካዊ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት የክልሉን ከተሞች የቦታ አጠቃቀምና ሥርዓታዊ ዕድገት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ስትራቴጂካዊ ተግባራትን ማከናወኑን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ ኃይሌ አስታውቀዋል። በበጀት ዓመቱ ባለፉት 6 ወራት ኢንስቲትዩቱ ለማዘጋጀት ካቀዳቸው 15 የፕላን ዓይነቶች መካከል 14ቱ ተጠናቀው ለተፈጻሚነት ዝግጁ መደረጋቸውን ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል። የከተማ…

Read More

በግማሽ ዓመቱ በብዙ መልኩ ውጤት የተመዘገበበት እና የአመራር የማስፈፀም አቅም እያደገ የመጣበት ነው -አቶ ፍቅሬ አማን

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል። በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የተከናወኑ የፓርቲ ስራዎች አፈፃፀም ሪፖርት እና የቀጣይ የትኩረት ግቦች ላይም ውይይት ተደርጓል። የ2017በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ተቋማት የዕውቅናና ማበረታቻ ሽልማት በማበርከት ደካማ አፈጻጸም ላስመዘገቡት ተቋማት እና ግለሰቦች…

Read More

መከላከል በምንችላቸው ምክንያቶች የእናቶች ህይወት እንዳያልፍ ሁሉም አካላት የድርሻቸውን መወጣት ይገባቸዋል፦የክልሉ ጤና ቢሮ

መከላከል በምንችላቸው ምክንያቶች የእናቶች ህይወት እንዳያልፍ ሁሉም አካላት የድርሻቸውን መወጣት እንደሚገባቸው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ አሳሰበ። ቢሮው “ፈጠራና ዘላቂ ፋይናንስ ለጤናማ እናትነት” በሚል መሪ ቃል የጤናማ እናትነት ወር ንቅናቄ መድረክ አካሂዷል። በንቅናቄ መድረኩ የተገኙት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም፤ መከላከል በምንችላቸው ምክንያቶች እናቶች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ሞት በመከላከል ሀላፊነታችንን ልንወጣ…

Read More

ኢትዮጵያ የቀጣናዊ ብልጽግና ሞተር እና የአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ማዕከል ናት- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ከሕልም ወደ እውነት፤ ኢትዮጵያ የቀጣናዊ ብልጽግና ሞተር እና የአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ማዕከል ናት ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። አገልግሎቱ ባወጣው መግለጫ፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ አዲስና ብሩኅ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች ብሏል። ትናንት ስናልማቸው የነበሩ ታላላቅ ርዕዮች ዛሬ በተግባር ተተርጉመው የዜጎች ተጠቃሚነት የሚረጋገጥባቸው፣ የሀገር ክብር የሚታደስባቸውና የቀጣናው ትስስር የሚጠናከርባቸው ኅያው እውነታዎች ሆነዋል ሲልም ገልጿል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ…

Read More

የሻይ ልማት ኢንሼቲቭን ተግባራትን በማጠናከር የገጠር ትራንስፎርሜሽን አጀንዳን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን በካፋ ዞን ገዋታ ወረዳ የቦጊንዳ ‎የሻይ ችግኝ ዝግጅት ጣቢያ ከአካባቢው ለተወጣጡ አርሶ አደሮችና የግብርና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል። ዓላማው የተዘጋጀውን የሻይ ቅጠል ችግኝን ከተከላ በፊት ከውጪው አየር ጋር በተገቢ ማላመድ፣ የመንከባከብና ከተላመደ በኃላ ወደ አርሶ አደሩ ማሳ በመውሰድ ለመትከል ከማሳ ልየታ እስከ ተከላና ምርት አሰባሰብ…

Read More

በሚዛን አማን ከተማ የሰንበት ገበያ ተጠናክሮ ቀጥሏል፤ ለገበያው መሳካት ከ2.8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል

​በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም እና ህብረተሰቡን በተመጣጣኝ ዋጋ ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመረው የሰንበት ገበያ፣ በሁለቱም ማዕከላት (ሚዛንና አማን) በልዩ ትኩረት ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ። ​የከተማ አስተዳደሩ የሰንበት ገበያን ዘላቂና ምቹ ለማድረግ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሰ ይገኛል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ በሚዛንና በአማን ለሚገኙ የገበያ ማዕከላት ከ2.8 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ግዙፍ የገበያ ድንኳኖች ግዥ…

Read More

የምክር ቤቶች የክትትልና ቁጥጥር ስራ በአስፈፃሚ አካላት ዘንድ ተጠያቂነትን በማስፈን የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውጤቶች እያስመዘገበ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ ገለጹ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የክልሉንና የዞኖች የ2018 በጀት አመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፃመ እየገመገመ ይገኛል፡፡ የግምገማ መድረኩን በንግግር የከፈቱ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ ምክር ቤቶች በሚያደርጉት የክትትትልና ቁጥጥር ስራዎች አስፈፃሚ ተቋማት በዕቅዳቸዉ መሠረት ተግባራትን በማከናወን የህብረተሰብ ተጠቃሚነት እንዲያሳድጉ በተከናወኑ ተግባራት ዉጤት እየተመዘገብ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ በግምገማ መድረኩ በህገ…

Read More

የሸበሌ ሪዞርት በዛሬው ዕለት በይፋ ተመረቀ

የሸበሌ ሪዞርት በዛሬው ዕለት በይፋ መመረቁን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታወቀ። ሪዞርቱ የገበታ ለትውልድ ዋነኛ ፕሮጀክት ሲሆን በ385 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው፡፡ በአንድ ጊዜ እስከ 400 እንግዶችን ማስተናገድ የሚችሉ ሦስት ምግብ ቤቶች፣ ልዩ የባሕል ማዕከል፣ ዘመናዊ የክብረ-በዓላትና የስብሰባ አዳራሾች፣ የሕፃናት መጫወቻ ስፍራዎችና 15.4 ኪሎ ሜትር የሚረዝሙ የእግረኛ መንገዶችን የያዘው የሸበሌ ሪዞርት፤ ማኅበራዊ ትስስርን ለማጠናከር ታሳቢ…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ እና ለሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሸክ ሞሃሙድ አቀባበል አደረጉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ እና ለሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሸክ ሞሃሙድ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመሪዎች አቀባበል ያደረጉት ዛሬ ጠዋት በጅግጅጋ አውሮፕላን ማረፊያ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል። #FMC

Read More