የዲጂታል ጤና አገልግሎቶችን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ጤንነቴ የሞባይል መተግበሪያ የኢፌድሪ ፕሬዝደንት ታዬ አስቃስላሴ በተገኙበት ይፋ ተደረገ
ጤና ሚኒስቴር “ጤንነቴ የሞባይል መተግበሪያን” በአዲስ አበባ የሳይንስ ሙዚየም በመካሄድ ላይ በሚገኘው የዲጂታል ጤና ኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽን የመክፈቻ መርሃግብር ላይ ይፋ አድርጓል። በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢትዮጲያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት፣ ታዬ አስቃስላሴ ጤንነቴ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ መሆኑን በመግለጽ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የተዘጋጀዉን የዲጂታል ጤና ኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽን በይፋ ከፍተዋል። መንግስት የጤናው ዘርፍን ለማሳደግ እየተሰሩ የሚገኙ…
